1 ሳሙኤል 7:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ታቦቲቱም በቂርያትይዓሪም ከተቀመጠችበት ቀን ጀምሮ ወራቱ ረዘመ፤ ሃያ ዓመትም ሆነ፤ የእስራኤልም ቤት ሁሉ አዝኖ እግዚአብሔርን ተከተለ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ታቦቱ በቂርያትይዓይሪም ከተቀመጠ ረዥም ጊዜ ሆነው፤ በአጠቃላይ ሃያ ዓመት ቈየ። የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ አዘነ፤ እግዚአብሔርንም ፈለገ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ታቦቱ በቂርያትይዓሪም ከተቀመጠ ረዥም ጊዜ ሆነው፤ ሃያ ዓመትም ያህል ኖረ። በዚያን ጊዜ የእስራኤል ቤት ሁሉ አዝኖ ጌታን ፈለገ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 የእግዚአብሔር ታቦት ለረዥም ጊዜ በቂርያትይዓሪም ኖረ፤ ይኸውም ኻያ ዓመት ያኽል ነበር፤ በዚህን ጊዜ እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር እጅግ አለቀሱ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ታቦቱም በቂርያትይዓሪም ከተቀመጠበት ቀን ጀምሮ ወራቱ ረዘመ፥ ሀያ ዓመትም ሆነ፥ የእስራኤልም ቤት ሁሉ አዝኖ እግዚአብሔርን ተከተለ። See the chapter |