Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 6:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የቤ​ት​ሳ​ሚ​ስም ሰዎች፥ “በዚህ በቅ​ዱሱ አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ማለፍ ማን ይች​ላል? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ከእኛ ወጥታ ወደ ማን ትሄ​ዳ​ለች?” አሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 የቤትሳሚስም ሰዎች፣ “ታዲያ በዚህ ቅዱስ አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ማን መቆም ይችላል? ታቦቱስ ከዚህ ወጥቶ ወደ ማን ይሂድ?” አሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የቤትሼሜሽም ሰዎች፥ “ታዲያ በዚህ ቅዱስ አምላክ በጌታ ፊት ማን መቆም ይችላል? ታቦቱስ ከዚህ ወጥቶ ወደ ማን ይሂድ?” አሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ስለዚህም የቤትሼሜሽ ሰዎች “በዚህ ቅዱስ አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ማን መቆም ይችላል? ታቦቱስ ከእኛ ወጥቶ ወደ ማን ይሄዳል?” አሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የቤትሳሚስም ሰዎች፦ በዚህ በቅዱስ አምላክ በእግዚአብሔር ፊት መቆም ማን ይችላል? ከእኛስ ወጥቶ ወደ ማን ይሄዳል? አሉ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 6:20
13 Cross References  

ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው?


በዚ​ያም ቀን ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈራና፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ወደ እኔ እን​ዴት ትገ​ባ​ለች?” አለ።


ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፤ ማንስ ሊቆም ይችላል?” አሉአቸው።


በጌ​ር​ጌ​ሴ​ኖ​ንም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ሄ​ድ​ላ​ቸው ማለ​ዱት፤ ጽኑ ፍር​ሀት ይዞ​አ​ቸ​ዋ​ልና፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በታ​ንኳ ሆኖ ተመ​ለሰ።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ይህን አይቶ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና፥ “እኔ ኀጢ​አ​ተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በውኑ ይጥ​ላ​ልን? እን​ግ​ዲ​ህስ ይቅ​ር​ታ​ውን አይ​ጨ​ም​ር​ምን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዖዛ ላይ ተቈጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያው ቀሠ​ፈው። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት አጠ​ገብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዚ​ያው ሞተ።


በም​ድ​ርም ላይ በሚ​ሳብ ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሁሉ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን አታ​ሳ​ድፉ። እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እሆን ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እን​ግ​ዲህ እኔ ቅዱስ ነኝና እና​ን​ተም ቅዱ​ሳን ሁኑ።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ቀድሱ፤ ቅዱ​ሳ​ንም ሁኑ፤ እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ነኝና፤


የአ​ዛ​ጦ​ንም ሰዎች እን​ዲህ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ፥ “እጁ በእ​ኛና በአ​ም​ላ​ካ​ችን በዳ​ጎን ላይ ጠን​ክ​ራ​ለ​ችና የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦት ከእኛ ዘንድ አት​ቀ​መጥ” አሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements