1 ሳሙኤል 4:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 በመጣም ጊዜ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ልቡ ተናውጦ ነበርና በመንገድ ዳር በወንበሩ ላይ ተቀምጦ ይጠባበቅ ነበር፤ ሰውዬውም ወደ ከተማዪቱ ገብቶ ባወራ ጊዜ ከተማዪቱ ሁሉ ተጭዋጭዋኸች። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 እዚያ እንደ ደረሰም፣ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ልቡ ስለ ተጨነቀ፣ በመንገድ ዳር ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ይጠባበቅ ነበር። ሰውየውም ወደ ከተማው ገብቶ የሆነውን ሁሉ ባወራ ጊዜ፣ ከተማው ሁሉ በጩኸት ተናወጠ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 እዚያ እንደደረሰም፥ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ልቡ ስለ ተጨነቀ፥ በመንገድ ዳር ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ይጠባበቅ ነበር። ሰውየውም ወደ ከተማው ገብቶ የሆነውን ሁሉ ባወራ ጊዜ፥ ከተማው ሁሉ በጩኸት ተናወጠ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ሰውዬው በደረሰ ጊዜ ልቡ ለእግዚአብሔር ታቦት ተጨንቆ የነበረው ዔሊ በመንገድ ዳር በወንበር ተቀምጦ ይመለከት ነበር። ሰውዬውም ወደ ከተማ መጥቶ ወሬውን በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ከፍተኛ ጩኸት አስተጋቡ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 በመጣም ጊዜ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ልቡ ተናውጦ ነበርና በመንገድ ዳር በወንበሩ ላይ ተቀምጦ ይጠባበቅ ነበር፥ ሰውዮውም ወደ ከተማይቱ ገብቶ ባወራ ጊዜ ከተማይቱ ሁሉ ተጭዋጭዋኽች። See the chapter |