Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 30:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ዳዊ​ትም፥ “ወደ እነ​ዚያ ሠራ​ዊት ልት​መ​ራኝ ትወ​ድ​ዳ​ለ​ህን?” አለው፥ እር​ሱም፥ “እን​ዳ​ት​ገ​ድ​ለኝ፥ ለጌ​ታ​ዬም እጅ አሳ​ል​ፈህ እን​ዳ​ት​ሰ​ጠኝ በአ​ም​ላክ ማል​ልኝ፤ እኔም ወደ እነ​ዚያ ሠራ​ዊት እመ​ራ​ሃ​ለሁ” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ዳዊትም፣ “ታዲያ ወራሪው ሰራዊት ወዳለበት መርተህ ታደርሰኛለህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “እንደማትገድለኝ ወይም ለጌታዬ አሳልፈህ እንደማትሰጠኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ እንጂ እነዚህ ወራሪዎች ወዳሉበት አደርስሃለሁ” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ዳዊትም፥ “ታዲያ ወራሪው ሠራዊት ወዳለበት መርተህ ትወስደኛለህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፥ “እንደማትገድለኝ ወይም ለጌታዬ አሳልፈህ እንደማትሰጠኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ እንጂ እነዚህ ወራሪዎች ወዳሉበት አደርስሃለሁ” አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ዳዊትም “እነዚያ ወራሪዎች ወዳሉበት ስፍራ ልትመራን ትችላለህን?” ሲል ጠየቀው። ወጣቱም “እንደማትገድለኝና ለጌታዬም አሳልፈህ እንደማትሰጠኝ ከማልክልኝ ላሳይህ እችላለሁ” ሲል መለሰለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ዳዊትም፦ ወደ እነዚያ ሠራዊት ዘንድ ልትመራኝ ትወድዳለህን? አለው፥ እርሱም፦ እንዳትገድለኝ፥ ለጌታዬም እጅ አሳልፈህ እንዳትሰጠኝ በአምላክ ማልልኝ እንጂ ወደ እነዚያ ሠራዊት እመራሃለሁ አለ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 30:15
12 Cross References  

ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝ! የና​ቀ​ውን መሐ​ላ​ዬ​ንና ያፈ​ረ​ሰ​ውን ቃል ኪዳ​ኔን በራሱ ላይ አመ​ጣ​ለሁ በላ​ቸው።


“እኔ ሕያው ነኝ! ያነ​ገ​ሠ​ውና መሐ​ላ​ውን የና​ቀ​በት፥ ቃል ኪዳ​ኑ​ንም ያፈ​ረ​ሰ​በት ንጉሥ በሚ​ኖ​ር​በት ስፍራ ከእ​ርሱ ጋር በባ​ቢ​ሎን መካ​ከል በር​ግጥ ይሞ​ታል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከመ​ን​ግ​ሥ​ትም ዘር ወስዶ ከእ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ አማ​ለ​ውም፤ የም​ድ​ሪ​ቱ​ንም ኀያ​ላን ወሰደ፤


አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን ጠርቶ፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! አንተ በፊቴ ጻድ​ቅና ደግ ነህ፤ ከእ​ኔም ጋር በጭ​ፍ​ራው በኩል መው​ጣ​ት​ህና መግ​ባ​ትህ በፊቴ መል​ካም ነው፤ ወደ እኔ ከመ​ጣህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ አን​ዳች ክፋት አላ​ገ​ኘ​ሁ​ብ​ህም፤ ነገር ግን በአ​ለ​ቆች ዘንድ አል​ተ​ወ​ደ​ድ​ህም።


ኢያ​ሱም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሰላም አደ​ረገ፤ በሕ​ይ​ወት እን​ዲ​ተ​ዋ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች ማሉ​ላ​ቸው።


አሁ​ንም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማሉ​ልኝ፤ እኔ ለእ​ና​ንተ ቸር​ነት እንደ አደ​ረ​ግሁ እና​ንተ ደግሞ ለአ​ባቴ ቤት ቸር​ነት እን​ድ​ታ​ደ​ርጉ፥ በእ​ው​ነት ምል​ክት ስጡኝ።


እኛም በከ​ሊ​ታ​ው​ያን አዜብ፥ በይ​ሁ​ዳም በኩል፥ በካ​ሌ​ብም አዜብ ላይ ዘመ​ትን፥ ሴቄ​ላ​ቅ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ል​ናት” አለው።


ወደ እዚ​ያም ባደ​ረ​ሰው ጊዜ፥ እነሆ፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንና ከይ​ሁዳ ምድር ከወ​ሰ​ዱት ከብዙ ምርኮ ሁሉ የተ​ነሣ በል​ተው፥ ጠጥ​ተው፥ የበ​ዓ​ልም ቀን አድ​ር​ገው፥ በም​ድር ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነው አገ​ኛ​ቸው።


“እጅ​ህን በእጄ ላይ አድ​ርግ፤ እኔም አብሬ ከም​ኖ​ራ​ቸው ከከ​ነ​ዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይ​ስ​ሐቅ ሚስት እን​ዳ​ት​ወ​ስ​ድ​ለት በሰ​ማ​ይና በም​ድር አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ል​ሃ​ለሁ፤


ጠባ​ቂ​ዎ​ቹም አንድ ሰው ከከ​ተማ ሲወጣ አይ​ተው ያዙ​ትና፥ “የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱን መግ​ቢያ አሳ​የን፤ እኛም ምሕ​ረት እና​ደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለን” አሉት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements