Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 30:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዳዊ​ትም፥ “አንተ የማን ነህ? ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። ያም ግብ​ፃዊ ብላ​ቴና፥ “እኔ የአ​ማ​ሌ​ቃዊ ባሪያ ነኝ፤ ከሦ​ስት ቀንም በፊት ታምሜ ነበ​ርና ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ዳዊትም፣ “አንተ የማን ነህ? የመጣኸውስ ከየት ነው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም እንዲህ አለው፤ “እኔ ግብጻዊ ስሆን፣ የአንድ አማሌቃዊ ባሪያ ነኝ፤ ከሦስት ቀን በፊት ታምሜ በነበረበት ጊዜ ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ዳዊትም፥ “አንተ የማን ነህ? የመጣኸውስ ከየት ነው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም እንዲህ አለው፤ “እኔ ግብፃዊ ስሆን፥ የአንድ አማሌቃዊ አገልጋይ ነኝ፤ ከሦስት ቀን በፊት ታምሜ በነበረበት ጊዜ ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ዳዊትም ወጣቱን “የማን አገልጋይ ነህ? አመጣጥህስ ከየት ነው?” ሲል ጠየቀው። ወጣቱም “እኔ ግብጻዊ የሆንኩ የአንድ ዐማሌቃዊ አገልጋይ ነኝ፤ ታምሜ ስለ ነበር ከሦስት ቀን በፊት ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ዳዊትም፦ አንተ የማን ነህ? ከወዴት መጣህ? አለው። እርሱም፦ እኔ የአማሌቃዊ ባሪያ ግብጻዊ ብላቴና ነኝ፥ ከሦስት ቀንም በፊት ታምሜ ነበርና ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 30:13
9 Cross References  

ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።


ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፤ የኃጥኣን ምሕረት ግን አለመመጽወት ነው።


ከበ​ለ​ሱም ጥፍ​ጥፍ ቍራጭ ሰጡ​ትና በላ፤ ነፍ​ሱም ወደ እርሱ ተመ​ለ​ሰች፤ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እን​ጀራ አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም ነበ​ርና።


እኛም በከ​ሊ​ታ​ው​ያን አዜብ፥ በይ​ሁ​ዳም በኩል፥ በካ​ሌ​ብም አዜብ ላይ ዘመ​ትን፥ ሴቄ​ላ​ቅ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ል​ናት” አለው።


እር​ሱም፦ አንተ ማን ነህ? አለኝ፤ እኔም አማ​ሌ​ቃዊ ነኝ ብዬ መለ​ስ​ሁ​ለት።


የዚ​ያን ጊዜም፥ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክ​ን​ያት እን​ዳ​ገ​ኘን እባ​ክህ ንገ​ረን፤ ሥራህ ምን​ድን ነው? ከወ​ዴ​ትስ መጣህ? ወዴ​ትስ ትሄ​ዳ​ለህ? ሀገ​ርህ የት ነው? ወገ​ን​ህስ ምን​ድን ነው?” አሉት።


ዳዊ​ትም፥ “ከወ​ዴት መጣህ?” አለው፤ እር​ሱም፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ሰፈር አም​ልጬ መጣሁ” አለው።


ዳዊ​ትም ወሬ​ውን ያመ​ጣ​ለ​ትን ጐል​ማሳ፥ “አንተ ከወ​ዴት ነህ?” አለው፤ እር​ሱም፥ “እኔ የመ​ጻ​ተ​ኛው የአ​ማ​ሌ​ቃ​ዊው ልጅ ነኝ” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements