Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 29:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ዳዊ​ትም አን​ኩ​ስን፥ “ምን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ? ሄጄስ ከጌ​ታዬ ከን​ጉሡ ጠላ​ቶች ጋር እን​ዳ​ል​ዋጋ፥ በፊ​ትህ ከተ​ቀ​መ​ጥሁ ጀምሬ እስከ ዛሬ ድረስ በእኔ በአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ምን በደል አግ​ኝ​ተ​ህ​ብ​ኛል?” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ዳዊትም አንኩስን፣ “ለመሆኑ ምን አደረግሁ? እዚህ ከመጣሁበት ዕለት ጀምሮ እስካሁን ድረስ፣ በአገልጋይህ ላይ ምን አገኘህበት? ታዲያ፣ ከንጉሡ ከጌታዬ ጠላቶች ጋራ የማልዋጋው ስለ ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ዳዊትም ለአኪሽ፥ “ለመሆኑ ምን አደረግሁ? እዚህ ከመጣሁበት ዕለት ጀምሮ እስካሁን ድረስ፥ በአገልጋይህ ላይ ምን አገኘህበት? ታዲያ፥ ከንጉሡ ከጌታዬ ጠላቶች ጋር የማልዋጋው ስለ ምንድነው?” ብሎ ጠየቀው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ዳዊትም “ጌታዬ ምን በደል ሠራሁ? አንተን ማገልገል ከጀመርኩበት ጊዜ አንሥቶ በደል ካልተገኘብኝ ጌታዬና ንጉሤ የሆንከውን አንተን ተከትዬ በመዝመት ጠላቶችህን መውጋት የማልችለው ስለምንድን ነው?” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ዳዊትም አንኩስን፦ ምን አድርጌአለሁ? ሄጄስ ከጌታዬ ከንጉሡ ጠላቶች ጋር እንዳልዋጋ፥ በፊትህ ከተቀመጥሁ ጀምሬ እስከ ዛሬ ድረስ በእኔ በባሪያህ ምን አግኝተህብኛል? አለው።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 29:8
10 Cross References  

ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።’


ዳዊ​ትም አን​ኩ​ስን፥ “አሁን አገ​ል​ጋ​ይህ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ንገ​ረው” አለው። አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “እን​ግ​ዲህ በዘ​መኑ ሁሉ ራሴን ጠባቂ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” አለው።


ደግ​ሞም አለ፥ “ጌታዬ አገ​ል​ጋ​ዩን ስለ​ምን ያሳ​ድ​ዳል? ምን አደ​ረ​ግሁ? ምንስ ክፋት በእጄ ላይ ተገ​ኘ​ብኝ?


እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ከባ​ሪ​ያህ ጋር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ለባ​ሪ​ያህ ቸር​ነ​ትን አድ​ርግ፤ በደል ግን ቢገ​ኝ​ብኝ አንተ ግደ​ለኝ፤ ለምን ወደ አባ​ትህ ታደ​ር​ሰ​ኛ​ለህ?”


ዳዊ​ትም፥ “እኔ ምን አደ​ረ​ግሁ? ይህ ታላቅ ነገር አይ​ደ​ለ​ምን?” አለ።


እነ​ሆኝ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና እርሱ በቀ​ባው ፊት መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ የማ​ንን በሬ ወሰ​ድሁ? የማ​ን​ንስ አህያ ወሰ​ድሁ? ማን​ንስ ሸነ​ገ​ልሁ? በማ​ንስ ላይ ግፍ አደ​ረ​ግሁ? ነጠላ ጫማ እን​ኳን ቢሆን ከማን እጅ መማ​ለጃ ተቀ​በ​ልሁ? መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ እኔ እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።”


አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመ​ታ​ችሁ?” አለው፤ ዳዊ​ትም፥ “በይ​ሁዳ ደቡብ፥ በያ​ሴ​ሜጋ ደቡብ፥ በቄ​ኔ​ዛ​ው​ያን ደቡብ ላይ ዘመ​ትን” አለው።


አሁ​ንም ተመ​ል​ሰህ በሰ​ላም ሂድ፤ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም አለ​ቆች ዐይን ክፋት አታ​ድ​ርግ” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements