Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 28:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ራ​ኤ​ልን ከአ​ንተ ጋር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል፤ ነገም አን​ተና ከአ​ንተ ጋር ያሉ ልጆ​ችህ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጭፍራ ደግሞ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እግዚአብሔር አንተንና እስራኤልን ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል፤ አንተና ልጆችህም ነገ ከእኔ ጋራ ትሆናላችሁ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር የእስራኤልን ሰራዊት ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ገና ጌታ አንተንና እስራኤልን ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል፤ አንተና ልጆችህም ነገ ከእኔ ጋር ትሆናላችሁ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር የእስራኤልን ሠራዊት ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ስለዚህ እርሱ አንተንና እስራኤልን ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣችኋል፤ ነገ አንተና ልጆችህ እኔ ወዳለሁበት ቦታ ትመጣላችሁ፤ እግዚአብሔርም የእስራኤልን ሠራዊት ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እግዚአብሔርም እስራኤልን ከአንተ ጋር በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፎ ይሰጣል፥ ነገም አንተና ልጆችህ ከእኔ ጋር ትሆናላችሁ፥ እግዚአብሔርም የእስራኤልን ጭፍራ ደግሞ በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፎ ይሰጣል።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 28:19
12 Cross References  

ሐና​ን​ያም ይህን በሰማ ጊዜ ወድቆ ሞተ፤ ጽኑ ፍር​ሀ​ትም ሆነ፤ የሰ​ሙ​ትም ሁሉ ፈሩ።


የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር፤” አለ።


ሚክ​ያ​ስም፥ “በሰ​ላም ብት​መ​ለስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ የተ​ና​ገረ አይ​ደ​ለም” አለ። ደግ​ሞም አሕ​ዛብ ሁሉ ሆይ! ስሙኝ” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ወጥቶ በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ ይወ​ድቅ ዘንድ አክ​ዓ​ብን የሚ​ያ​ሳ​ስት ማን ነው? አለ። አን​ዱም እን​ዲህ ያለ ነገር፥ ሌላ​ውም እን​ዲያ ያለ ነገር ተና​ገረ።


ነገር ግን ክፉ ብት​ሠሩ እና​ን​ተም፥ ንጉ​ሣ​ች​ሁም ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።”


እነሆ፥ ከተ​መ​ሠ​ረ​ተች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ በግ​ብፅ ሆኖ የማ​ያ​ውቅ እጅግ ታላቅ በረዶ ነገ በዚህ ጊዜ አዘ​ን​ባ​ለሁ።


ሳኦ​ልም በዚያ ጊዜ በቁ​መቱ ሙሉ በም​ድር ላይ ወደቀ፤ ከሳ​ሙ​ኤ​ልም ቃል የተ​ነሣ እጅግ ፈራ። በዚ​ያም ቀን ሁሉ፥ በዚ​ያም ሌሊት ሁሉ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ምና ኀይል አል​ቀ​ረ​ለ​ትም።


ኃጥ​ኣን በዚያ በቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ በዚ​ያም በሥ​ጋ​ቸው የተ​ጨ​ነ​ቁት ያር​ፋሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements