Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 28:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሳኦ​ልም ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በዚህ ነገር ክፉ አያ​ገ​ኝ​ሽም ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማለ​ላት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሳኦልም፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! በዚህ ነገር ቅጣት አያገኝሽም” ሲል በእግዚአብሔር ስም ማለላት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከዚያም ሳኦል “በዚህ ነገር ምንም ዓይነት ቅጣት እንደማይደርስብሽ በሕያው ጌታ ስም ምዬ ቃል እገባልሻለሁ” ሲል በጌታ ስም ማለላት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከዚያም በኋላ ሳኦል “በዚህ ነገር ምንም ዐይነት ቅጣት እንደማይደርስብሽ በሕያው እግዚአብሔር ስም ምዬ ቃል እገባልሻለሁ” አላት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ሳኦልም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! በዚህ ነገር ቅጣት አያገኝሽም ብሎ በእግዚአብሔር ማለላት።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 28:10
10 Cross References  

“የመንግሥቴ እኩሌታ ስንኳ ቢሆን የምትለምኚውን ሁሉ እሰጥሻለሁ፤” ብሎ ማለላት።


ዳግመኛም ሲምል “ሰውየውን አላውቀውም፤” ብሎ ካደ።


ያችም ሴት፥ “ለመ​ግ​ደል ባለ ደሞች እን​ዳ​ይ​በዙ፤ ልጄ​ንም እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉ​ብኝ ንጉሥ ፈጣ​ሪው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያስብ” አለች። እር​ሱም፥ “የል​ጅ​ሽስ አን​ዲት የራሱ ጠጕር በም​ድር ላይ እን​ዳ​ት​ወ​ድቅ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን” አላት።


ሳኦ​ልም የዮ​ና​ታ​ንን ቃል ሰማ፤ ሳኦ​ልም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዳዊት አይ​ገ​ደ​ልም” ብሎ ማለ።


እስ​ራ​ኤ​ልን የሚ​ያ​ድን ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ኀጢ​ኣቱ በልጄ በዮ​ና​ታን ቢሆን ፈጽሞ ይሞ​ታል” አለ። ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ አንድ የመ​ለ​ሰ​ለት ሰው አል​ነ​በ​ረም።


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ክ​ህን ስም በከ​ንቱ አት​ጥራ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙን በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ራ​ውን ከበ​ደል አያ​ነ​ጻ​ው​ምና።


ከእ​ር​ስዋ በበ​ላ​ችሁ ቀን፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ እን​ዲ​ከ​ፈቱ፥ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ም​ት​ሆኑ፥ መል​ካ​ም​ንና ክፉን እን​ደ​ም​ታ​ውቁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ​ሚ​ያ​ውቅ ነው እንጂ።”


ሴቲ​ቱም፥ “እነሆ፥ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ከም​ድር እን​ዳ​ጠፋ ሳኦል ያደ​ረ​ገ​ውን ታው​ቃ​ለህ፤ ስለ​ምን እኔን ለማ​ስ​ገ​ደል ለነ​ፍሴ ወጥ​መድ ታደ​ር​ጋ​ለህ?” አለ​ችው።


ሴቲ​ቱም፥ “ማንን ላስ​ነ​ሣ​ልህ?” አለ​ችው፤ እር​ሱም፥ “ሳሙ​ኤ​ልን አስ​ነ​ሽ​ልኝ” አላት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements