Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 27:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከነ​ቤ​ተ​ሰቡ ከአ​ን​ኩስ ጋር በጌት ተቀ​መጡ፤ ከዳ​ዊ​ትም ጋር ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ አኪ​ና​ሆ​ምና የቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊው የና​ባል ሚስት አቤ​ግያ ሁለቱ ሚስ​ቶቹ ነበሩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ዳዊትና ሰዎቹ በጋት በአንኩስ ዘንድ ተቀመጡ፤ እያንዳንዱ ሰው ከቤተ ሰቡ ጋራ ነበረ፤ ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ጋራ፣ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆምና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ አቢግያ ጋራ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ዳዊትና ሰዎቹ በጋት በአኪሽ ዘንድ ተቀመጡ፤ እያንዳንዱ ሰው ከቤተሰቡ ጋር ነበረ፤ ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ጋር፥ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአሒኖዓም እና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ አቢጌል ጋር ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ዳዊትና ተከታዮቹም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በጋት ተቀመጡ፤ ከዳዊትም ጋር ሁለቱ ሚስቶቹ አብረው ነበሩ፤ እነርሱም የኢይዝራኤል ተወላጅ የሆነችው አሒኖዓምና የቀርሜሎሱ ተወላጅ ናባል አግብቶአት የነበረው አቢጌል ነበሩ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ዳዊትና ሰዎቹም እያንዳንዳቸው ከነ ቤተ ሰቡ ከአንኩስ ጋር በጌት ውስጥ ተቀመጡ፥ ከዳዊትም ጋር ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት አቢግያ ሁለቱ ሚስቶቹ ነበሩ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 27:3
7 Cross References  

የዳ​ዊ​ትም ሁለቱ ሚስ​ቶቹ ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ አኪ​ና​ሆ​ምና የቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊው የና​ባል ሚስት የነ​በ​ረ​ችው አቤ​ግያ ተማ​ር​ከው ነበር።


ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወደ ከተማ በመጡ ጊዜ፥ እነሆ፥ በእ​ሳት ተቃ​ጥላ፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ተማ​ር​ከው አገኙ።


የሰ​ው​ዬ​ውም ስም ናባል፥ የሚ​ስ​ቱም ስም አቤ​ግያ ነበረ፤ ሴቲ​ቱም ደግና ብልህ፥ መል​ክ​ዋም እጅግ የተ​ዋበ ነበረ፤ ሰው​ዬው ግን ጨካ​ኝና ንፉግ ነበረ፤ ግብ​ሩም ክፉ ነበረ።


ለሳ​ኦ​ልም ዳዊት ወደ ጌት እንደ ኰበ​ለለ ነገ​ሩት፤ ከዚ​ያም በኋላ ደግሞ አል​ፈ​ለ​ገ​ውም።


ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሰዎች ሁሉ ከቤተ ሰባ​ቸው ጋር ወጡ፤ በኬ​ብ​ሮ​ንም ከተ​ሞች ተቀ​መጡ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements