Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 27:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ዳዊት እን​ዲህ አደ​ረገ፤ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሀገር በሚ​ቀ​መ​ጥ​በት ዘመን ሁሉ ልማዱ ይህ ነበረ ብለው እን​ዳ​ይ​ና​ገ​ሩ​ብን ብሎ ዳዊት ወደ ጌት ያመ​ጣ​ቸው ዘንድ ወን​ድም ሆነ ሴትም ሆነ ማን​ንም በሕ​ይ​ወት አል​ተ​ወም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ዳዊት “ ‘እርሱ እንዲህ አድርጓል’ ብለው ይነግሩብናል” ብሎ ስላሰበ፣ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አስቀርቶ ወደ ጋት አላመጣም። በፍልስጥኤም ግዛት በኖረበት ዘመን ሁሉ፣ እንዲህ ማድረጉ የተለመደ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ዳዊት “ ‘እርሱ እንዲህ አድርጓል’ ብለው ይነግሩብናል” ብሎ ስላሰበ፥ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አስቀርቶ ወደ ጋት አላመጣም። በፍልስጥኤም ግዛት በኖረበት ዘመን ሁሉ እንዲህ ማድረጉ የተለመደ ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ዳዊት ወንድንም ሆነ ሴትን ወደ ጋት ሳያመጣ ሁሉንም ገደለ። ይህንንም ያደረገው ዳዊት ይህንንና ይህንን አደረገ ብለው እንዳይነግሩበት ነው። በፍልስጥኤም አገር በኖረበት ዘመን ሁሉ ይህን የማድረግ ልማድ ነበረው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ዳዊት እንዲህ አደረገ በፍልስጥኤማውያንም አገር በሚቀመጥበት ዘመን ሁሉ ልማዱ ይህ ነበረ ብለው እንዳይናገሩብን ብሎ ዳዊት ወደ ጌት ያመጣቸው ዘንድ ወንድም ሆነ ሴትም ሆነ ማንንም በሕይወት አልተወም።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 27:11
7 Cross References  

የጻድቃን ከንፈሮች ምስክርነትን ያቀናሉ፥ የሚቸኩል ምስክር ግን ክፉ አንደበት አለው።


ዳዊት አብ​ያ​ታ​ርን፦ ሶር​ያ​ዊው ዶይቅ በዚያ መኖ​ሩን ባየሁ ጊዜ፥ “ለሳ​ኦል በር​ግጥ ይነ​ግ​ራል ብዬ በዚያ ቀን አው​ቄ​ዋ​ለሁ፤ ለአ​ባ​ትህ ቤት ነፍስ ሁሉ ጥፋት በደ​ለ​ኛው እኔ ነኝ።


አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመ​ታ​ችሁ?” አለው፤ ዳዊ​ትም፥ “በይ​ሁዳ ደቡብ፥ በያ​ሴ​ሜጋ ደቡብ፥ በቄ​ኔ​ዛ​ው​ያን ደቡብ ላይ ዘመ​ትን” አለው።


አን​ኩ​ስም፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ እጅግ የተ​ጠላ ሆኖ​አል፤ ስለ​ዚ​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባሪያ ይሆ​ነ​ኛል” ብሎ ዳዊ​ትን አመ​ነው።


ሴቶ​ቹ​ንና በው​ስ​ጥ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን ሁሉ ከታ​ናሽ እስከ ታላቅ ድረስ ማር​ከው ነበር፤ ሁሉ​ንም ወስ​ደው መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ሄዱ እንጂ ሴቶ​ች​ንም ሆነ ወን​ዶ​ችን አል​ገ​ደ​ሉም።


እስ​ማ​ኤል ማንም ሳያ​ውቅ ጎዶ​ል​ያ​ስን ከገ​ደለ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ቀን እን​ዲህ ሆነ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements