Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 26:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ዳዊ​ትም አቤ​ኔ​ርን፥ “አንተ ጐል​ማሳ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አን​ተን የሚ​መ​ስል ማን ነው? ጌታ​ህን ንጉ​ሡን ለመ​ግ​ደል አንድ ሰው ገብቶ ነበ​ርና ጌታ​ህን ንጉ​ሡን የማ​ት​ጠ​ብቅ ስለ​ምን ነው?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ዳዊትም ለአበኔር እንዲህ አለ፤ “አንተ ብርቱ ሰው ነህ? በእስራኤልስ ዘንድ አንተን የሚመስል ማን ነው? እነሆ፤ አንድ ሰው ንጉሡን ጌታህን ለመግደል መጥቶ ነበር፤ ታዲያ አንተ ንጉሥ ጌታህን ያልጠበቅኸው ስለ ምንድን ነው?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ዳዊትም እንዲህ አለ፤ “አንተ ብርቱ ሰው አይደለህምን? በእስራኤልስ ዘንድ አንተን የሚመስል ማን ነው? እነሆ፤ አንድ ሰው ንጉሡን ጌታህን ለመግደል መጥቶ ነበር፤ ታዲያ አንተ ንጉሥ ጌታህን ያልጠበቅኸው ስለ ምንድነው?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ዳዊትም “አበኔር! አንተ በእስራኤል የታወቅህ ታላቅ ሰው አይደለህምን? ታዲያ ጌታህን ንጉሡን በደንብ የማትጠብቀው ስለምንድን ነው? እነሆ፥ ከእኛ አንድ ሰው ጌታህን ለመግደል ወደ ሰፈር ገብቶ ነበር፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ዳዊትም አበኔርን፦ አንተ ጕልማሳ አይደለህምን? በእስራኤል ዘንድ አንተን የሚመስል ማን ነው? ጌታህን ንጉሡን ለመግደል አንድ ሰው ገብቶ ነበርና ጌታህን ንጉሡን የማትጠብቅ ስለ ምን ነው?

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 26:15
5 Cross References  

ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡ​ንና የኔር ልጅ አቤ​ኔ​ርን ጠራ​ቸው፥ “አቤ​ኔር ሆይ፥ አት​መ​ል​ስ​ምን?” አለው። አቤ​ኔ​ርም መልሶ፥ “አንተ የም​ት​ጠ​ራኝ ማን ነህ?” አለ።


ይህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ነገር መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባ​ውን ጌታ​ች​ሁን አል​ጠ​በ​ቃ​ች​ሁ​ምና ሞት ይገ​ባ​ች​ኋል፤ አሁ​ንም የን​ጉሡ ጦርና በራሱ አጠ​ገብ የነ​በ​ረው የውኃ መን​ቀል የት እንደ ሆነ ተመ​ል​ከት” አለው።


ንጉ​ሡም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ዛሬ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ታላቅ መኰ​ንን እንደ ወደቀ አታ​ው​ቁ​ምን?


ወደ ደቀ መዛሙርቱም መጣ፤ ተኝተውም አገኛቸውና ጴጥሮስን “እንዲሁም ከእኔ ጋር አንዲት ሰዓት እንኳ ልትተጉ አልቻላችሁምን?


Follow us:

Advertisements


Advertisements