Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 25:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 በነ​ጋ​ውም የወ​ይኑ ስካር ከና​ባል ባለፈ ጊዜ ሚስቱ ይህን ነገር ነገ​ረ​ችው፤ ልቡም በው​ስጡ ሞተ፤ እንደ ድን​ጋ​ይም ሆነ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 በነጋታውም የወይን ጠጅ ስካሩ ካለፈለት በኋላ ሚስቱ የሆነውን ሁሉ ለናባል ስትነግረው ልቡ ቀጥ አለ፤ ሰውነቱም እንደ ድንጋይ በድን ሆነ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ነግቶ የወይን ጠጁ ስካር ካለፈለት በኋላ የሆነውን ሁሉ ስትነግረው ልቡ ቀጥ አለ፤ ሰውነቱም እንደ ድንጋይ በድን ሆነ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 በማግስቱም ስካሩ ከበረደለት በኋላ ሁሉንም ነገር አስረዳችው፤ ልቡም በድንጋጤ ስለ ተመታ እንደ ድንጋይ ሆነ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 በነጋውም የጠጁ ስካር ከናባል ባለፈ ጊዜ ሚስቱ ይህን ነገር ነገረችው፥ ልቡም በውስጡ ሞተ፥

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 25:37
7 Cross References  

ነገር ግን ክፉ እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግ​ብሽ የከ​ለ​ከ​ለኝ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እኔን ለመ​ገ​ና​ኘት ፈጥ​ነሽ ባል​መ​ጣሽ ኖሮ፥ እስ​ኪ​ነጋ ድረስ ለና​ባል አጥር ተጠ​ግቶ የሚ​ሸን አንድ ስንኳ ባል​ቀ​ረ​ውም ብዬ ነበር።”


ለና​ባ​ልም ከሆ​ነው ሁሉ እስከ ነገ ጥዋት ድረስ አጥር ተጠ​ግቶ የሚ​ሸን አንድ ስንኳ ብን​ተው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዳ​ዊት ላይ እን​ዲህ ያድ​ርግ፤ እን​ዲ​ህም ይጨ​ምር” ብሎ ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዕ​ብ​ደት፥ በዕ​ው​ር​ነት፥ በልብ ድን​ጋ​ጤም ይመ​ታ​ሃል።


አቤ​ግ​ያም ወደ ናባል መጣች፤ እነ​ሆም፥ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ ያደ​ርግ ነበር፤ ናባ​ልም እጅግ ሰክሮ ነበ​ርና ልቡ ደስ ብሎት ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም እስ​ኪ​ነጋ ድረስ ታናሽ ነገር ወይም ታላቅ ነገር አል​ነ​ገ​ረ​ች​ውም ነበር።


ከዐ​ሥር ቀንም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናባ​ልን ቀሠ​ፈው፤ እር​ሱም ሞተ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements