Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 25:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ለና​ባ​ልም ከሆ​ነው ሁሉ እስከ ነገ ጥዋት ድረስ አጥር ተጠ​ግቶ የሚ​ሸን አንድ ስንኳ ብን​ተው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዳ​ዊት ላይ እን​ዲህ ያድ​ርግ፤ እን​ዲ​ህም ይጨ​ምር” ብሎ ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ነገ ጧት የርሱ ከሆነው ሁሉ አንድ ወንድ እንኳ በሕይወት ባስቀር እግዚአብሔር በዳዊት ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ያድርግበት፣ ከዚህም የከፋ ይጨምርበት!”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ነገ ጠዋት የእርሱ ከሆነው ሁሉ አንድ ወንድ እንኳ በሕይወት ባስቀር እግዚአብሔር በዳዊት ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ያድርግበት፥ ከዚህም የከፋ ይጨምርበት!”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከመንጋቱ በፊት የእርሱ የሆኑትን ወንዶች ሁሉ አንድ እንኳ ሳላስቀር በሙሉ ሳልገድል ብቀር እግዚአብሔር እኔን በሞት ይቅጣኝ!”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ለእርሱም ከሆነው ሁሉ እስከ ነገ ጥዋት ድረስ አንድ ወንድ ስንኳ ብተው እግዚአብሔር በዳዊት ላይ እንዲህ ያድርግ እንዲህም ይጨምር ብሎ ነበር።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 25:22
9 Cross References  

ስለ​ዚህ እነሆ፥ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ላይ መከ​ራን አመ​ጣ​ለሁ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ም​ንም አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ፤ አጥር ተጠ​ግቶ እስ​ከ​ሚ​ሸን ወንድ ድረስ አላ​ስ​ቀ​ር​ለ​ትም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ይነ​ግሥ ዘንድ አል​ተ​ወ​ውም፤ ሰው ገለባ እስ​ኪ​ያ​ልቅ ድረስ እን​ደ​ሚ​ያ​ነ​ድድ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ላይ እሳ​ትን አነ​ዳ​ለሁ።


አባ​ቴም በአ​ንተ ላይ ክፋት ማድ​ረግ ቢወ​ድድ፥ እኔም ባላ​ስ​ታ​ው​ቅህ፥ በሰ​ላ​ምም ትሄድ ዘንድ ባላ​ሰ​ና​ብ​ትህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዮ​ና​ታን ይህን ያድ​ርግ፤ ይህ​ንም ይጨ​ምር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ባቴ ጋር እንደ ነበረ ከአ​ንተ ጋር ይሁን።


እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የነ​ገ​ረህ ነገር ምን​ድን ነው? ከእኔ አት​ሸ​ሽግ፤ ከነ​ገ​ረ​ህና ከሰ​ማ​ኸው ነገር ሁሉ የሸ​ሸ​ግ​ኸኝ እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ያድ​ር​ግ​ብህ፤ እን​ዲ​ህም ይጨ​ም​ር​ብህ” አለው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ወጥቶ ፈረ​ሶ​ቹ​ንና ሰረ​ገ​ሎ​ቹን ያዘ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ን​ንም በታ​ላቅ አገ​ዳ​ደል ገደ​ላ​ቸው።


የአ​ክ​ዓ​ብን ቤት ሁሉ ታጠ​ፋ​ለህ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ አጥር ተጠ​ግቶ እስ​ከ​ሚ​ሸን የቀ​ረ​በ​ውን ሁሉና ከእ​ነ​ርሱ የቀ​ረ​ውን ሁሉ ታጠ​ፋ​ለህ።


ከነ​ገ​ሠና በዙ​ፋ​ኑም ከተ​ቀ​መጠ በኋላ፥ የባ​ኦ​ስን ቤት ሁሉ አጠፋ፤ አንድ ወንድ እንኳ አላ​ስ​ቀ​ረ​ለ​ትም።


ዮና​ታ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዳ​ዊት ጠላ​ቶች እጅ ይፈ​ል​ገው” ብሎ ከዳ​ዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ።


ሳኦ​ልም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ያድ​ር​ግ​ብኝ፤ እን​ዲ​ህም ይጨ​ም​ር​ብኝ፤ ዛሬ ፈጽ​መህ ትሞ​ታ​ለህ” አለ።


በምትሞችበትም ስፍራ እሞታለሁ፥ በዚያም እቀበራለሁ፣ ከሞት በቀር አንቺንና እኔን አንዳች ቢለየን እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ እንዲሁም ይጨምርብኝ አለች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements