1 ሳሙኤል 24:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የዳዊትም ሰዎች፥ “እነሆ፥ ጠላትህን በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፤ በዐይንህም ደስ የሚያሰኝህን ታደርግበታለህ ብሎ እግዚአብሔር የነገረህ ቀን እነሆ ዛሬ ነው” አሉት። ዳዊትም ተነሥቶ የሳኦልን መጐናጸፊያ ዘርፍ በቀስታ ቈረጠ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ዳዊት የሳኦልን ልብስ ጫፍ በመቍረጡ ልቡ በሐዘን ተመታ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 የዳዊት ሰዎችም ዳዊትን፥ “ጌታ፥ ‘የወደድኸውን ታደርግበት ዘንድ ጠላትህን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ’ ብሎ ለአንተ የተናገረው ቀን ዛሬ ነው” አሉት። ዳዊትም በልቡ እየተሳበ ሄዶ የሳኦልን ልብስ ጫፍ ማንም ሳያውቅ ቆርጦ ወሰደ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ነገር ግን ዳዊትን የኅሊና ወቀሳ አስጨነቀው፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ከዚያም በኋላ እንዲህ ሆነ፥ የሳኦልን የልብሱን ዘርፍ ስለቆረጠ የዳዊት ልብ በኅዘን ተመታ። See the chapter |