1 ሳሙኤል 24:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ሳኦልም ከእስራኤል ሁሉ የተመረጡትን ሦስት ሺህ ሰዎች ወሰደ፤ ዳዊትንና ሰዎቹንም ለመፈለግ ዋሊያዎች ወደሚታደኑባቸው ዓለቶች ሄደ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ሳኦልም በመንገድ ዳር ወዳለው ወደ አንድ የበጎች ማደሪያ በደረሰ ጊዜ፣ ዋሻ አግኝቶ ወገቡን ሊሞክር ወደዚያ ገባ። ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ስለዚህ ሳኦል ከመላው እስራኤል የተመረጡ ሦስት ሺህ ሰዎችን ይዞ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመፈለግ “የሜዳ ፍየሎች ዓለት” ወደ ተባለው ቦታ አቅራቢያ ሄደ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 በመንገድ ዳር ባሉት የበጎች ማደሪያዎች አቅራቢያ ወደሚገኘው ወደ አንድ ዋሻ ወገቡን ሊሞክር ወደ ውስጥ ገባ፤ በዚያም እርሱ ከተቀመጠበት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ዳዊትና ተከታዮቹ ተደብቀው የሚኖሩበት ክፍል ነበር፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 በመንገድም አጠገብ ወዳሉት የበጎች ማደሪያዎች መጣ፥ በዚያም ዋሻ ነበረ፥ ሳኦልም ወገቡን ይሞክር ዘንድ ከዚያ ገባ፥ ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር። See the chapter |