Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 23:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ፤ ዳዊ​ትም በቄኒ ውስጥ ተቀ​መጠ፤ ዮና​ታ​ንም ወደ ቤቱ ሄደ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረጉ። ከዚያም ዮናታን ወደ ቤቱ ሄደ፤ ዳዊት ግን እዚያው ሖሬሽ ተቀመጠ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሁለቱም በጌታ ፊት ቃል ኪዳን አደረጉ። ከዚያም ዮናታን ወደ ቤቱ ሄደ፤ ዳዊት ግን እዚያው ሖሬሽ ተቀመጠ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ስለዚህ ሁለቱም እርስ በርሳቸው የወዳጅነት ቃል ኪዳን አደረጉ፤ ከዚህም በኋላ ዳዊት በሖሬሽ መኖሩን ቀጠለ፤ ዮናታንም ወደ ቤቱ ተመልሶ ሄደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረጉ፥ ዳዊትም በጥሻው ውስጥ ተቀመጠ፥ ዮናታንም ወደ ቤቱ ሄደ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 23:18
8 Cross References  

ንጉ​ሡም በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል፥ በዳ​ዊ​ትና በሳ​ኦል ልጅ በዮ​ና​ታን መካ​ከል ስለ ነበ​ረው ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሐላ የሳ​ኦ​ልን ልጅ የዮ​ና​ታ​ንን ልጅ ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴን ራራ​ለት።


ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን፥ “በሰ​ላም ሂድ፤ እነሆ፥ እኛ ሁለ​ታ​ችን በእ​ኔና በአ​ንተ፥ በዘ​ሬና በዘ​ርህ መካ​ከል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ምስ​ክር ይሁን ብለን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ተማ​ም​ለ​ናል” አለው። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ዮና​ታ​ንም ወደ ከተማ ገባ።


ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ስለ ወደ​ደው ዮና​ታ​ንና ዳዊት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ።


ዳዊ​ትም፥ “ስለ ዮና​ታን ቸር​ነት አደ​ር​ግ​ለት ዘንድ ከሳ​ኦል ቤት የቀረ አንድ ሰው አለን?” አለ።


እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ከባ​ሪ​ያህ ጋር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ለባ​ሪ​ያህ ቸር​ነ​ትን አድ​ርግ፤ በደል ግን ቢገ​ኝ​ብኝ አንተ ግደ​ለኝ፤ ለምን ወደ አባ​ትህ ታደ​ር​ሰ​ኛ​ለህ?”


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ለሳ​ኦል መን​ገ​ሩን በፈ​ጸመ ጊዜ የዮ​ና​ታን ነፍስ በዳ​ዊት ነፍስ ታሰ​ረች፤ ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ወደ​ደው።


ዳዊ​ትም ወደ ካህኑ ወደ አቤ​ሜ​ሌክ ወደ ኖብ መጣ፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክም እር​ሱን በተ​ገ​ና​ኘው ጊዜ ደነ​ገጠ፥ “ስለ​ምን አንተ ብቻ​ህን ነህ? ከአ​ን​ተስ ጋር ስለ​ምን ማንም የለም?” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements