Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 23:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የቂ​አላ ሰዎ​ችስ ይከ​በ​ባ​ሉን? ባሪ​ያ​ህስ እንደ ሰማ ሳኦል በውኑ ይወ​ር​ዳ​ልን? የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ! ለባ​ር​ያህ ንገ​ረው” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይወ​ር​ዳል” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የቅዒላ ገዦች አሳልፈው ይሰጡኝ ይሆን? ባሪያህ እንደሰማውም ሳኦል ወደዚህ ይወርድ ይሆን? የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለባሪያህ እንድትነግረው እለምንሃለሁ።” እግዚአብሔርም፣ “አዎን ይወርዳል” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የቅዒላ ሰዎች አሳልፈው ይሰጡኝ ይሆን? ባርያህ እንደሰማውም ሳኦል ወደዚህ ይወርድ ይሆን? የእስራኤል አምላክ ጌታ ሆይ፤ ለአገልጋይህ እንድትነግረው እለምንሃለሁ።” ጌታም፥ “አዎን ይወርዳል” አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ታዲያ፥ የቀዒላ ከተማ ነዋሪዎች እኔን ለሳኦል አሳልፈው ይሰጡኝ ይሆን? ሳኦልስ እኔ እንደ ሰማሁት ወደዚህ መምጣቱ እውነት ነውን? የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! መልስ እንድትሰጠኝ እለምንሃለሁ!” እግዚአብሔርም “አዎ፥ ሳኦል በእርግጥ ይመጣል” ሲል መለሰለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የቅዒላ ሰዎች በእጁ አሳልፈው ይሰጡኛልን? ባሪያህስ እንደ ሰማ ሳኦል በውኑ ይወርዳልን? የእስራኤል አምላክ አቤቱ፥ እንድትነግረኝ እለምንሃለሁ አለ። እግዚአብሔርም፦ ይወርዳል አለ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 23:11
6 Cross References  

ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም የማ​ታ​ው​ቀ​ውን ታላ​ቅና ኀይ​ለኛ ነገ​ርን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።


አቤቱ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን ክፈት፥ አፌም ምስ​ጋ​ና​ህን ያወ​ራል።


ዳዊ​ትም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ! በእኔ ምክ​ን​ያት ከተ​ማ​ዪ​ቱን ያጠፋ ዘንድ ሳኦል ወደ ቂአላ ሊመጣ እን​ደ​ሚ​ፈ​ልግ እኔ ባሪ​ያህ ፈጽሜ ሰም​ቻ​ለሁ።


ዳዊ​ትም፥ “የቂ​አላ ሰዎች እኔ​ንና ሰዎ​ቼን በሳ​ኦል እጅ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ና​ልን?” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​አ​ች​ኋል” ብሎ ተና​ገረ።


ጌታ ሆይ! አስ​ታ​ው​ቀኝ፤ እኔም አው​ቃ​ለሁ፤ ያን​ጊ​ዜም ሥራ​ቸ​ውን ገለ​ጥ​ህ​ልኝ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements