Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 22:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እን​ግ​ዲህ ወዲህ ከእኔ ጋር ተቀ​መጥ፤ አት​ፍራ፤ ለእኔ ነፍስ የደ​ኅ​ን​ነት ቦታን እን​ደ​ም​ፈ​ልግ ለአ​ን​ተም ነፍስ የደ​ኅ​ን​ነት ቦታን እፈ​ል​ጋ​ለ​ሁና፥ ከእ​ኔም ጋር ተጠ​ብ​ቀህ ትኖ​ራ​ለህ” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አሁንም ከእኔ ጋራ ቈይ፤ አትፍራ፤ የአንተን ሕይወት የሚፈልግ የእኔን ሕይወት የሚፈልግ ነውና። ዐብረኸኝ በሰላም ትኖራለህ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 አሁንም ከእኔ ጋር ቆይ፤ አትፍራ፤ የአንተን ሕይወት የሚፈልግ የእኔን ሕይወት ይፈልጋል። አብረኸኝ በሰላም ትኖራለህ።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አንተ ግን ከእኔ ጋር ኑር፤ አይዞህ አትፍራ፤ በእርግጥ ሳኦል አንተንም እኔንም ለመግደል ይፈልጋል፤ ነገር ግን አንተ ከእኔ ጋር በሰላም ትኖራለህ” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ነፍሴን የሚፈልግ የአንተን ነፍስ ይፈልጋልና፥ ከእኔም ጋር ተጠብቀህ ትኖራለህና በእኔ ዘንድ ተቀመጥ፥ አትፍራ አለው።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 22:23
11 Cross References  

ንጉ​ሡም ካህ​ኑን አብ​ያ​ታ​ርን፥ “አንተ ዛሬ የሞት ሰው ነበ​ርህ፤ ነገር ግን የአ​ም​ላ​ክን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት በአ​ባቴ በዳ​ዊት ፊት ስለ ተሸ​ከ​ምህ፥ አባ​ቴም የተ​ቀ​በ​ለ​ውን መከራ ሁሉ አንተ ስለ ተቀ​በ​ልህ አል​ገ​ድ​ል​ህ​ምና በዓ​ና​ቶት ወዳ​ለው ወደ እር​ሻህ ፈጥ​ነህ ሂድ” አለው።


ይህም፥ “ከእ​ነ​ዚህ ከሰ​ጠ​ኸኝ አንድ ስንኳ አል​ጠ​ፋም” ያለው ቃሉ ይፈ​ጸም ዘንድ ነው።


እኔ፦ ከጌ​ታው የሚ​በ​ልጥ አገ​ል​ጋይ የለም ያል​ኋ​ች​ሁን ቃሌን ዐስቡ፤ እኔን ካሳ​ደዱ እና​ን​ተ​ንም ያሳ​ድ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ቃሌን ጠብ​ቀው ቢሆ​ንስ ቃላ​ች​ሁ​ንም በጠ​በቁ ነበር።


እኔ በዓ​ለም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሳለሁ ግን የሰ​ጠ​ኸ​ኝን በስ​ምህ እጠ​ብ​ቃ​ቸው ነበር፤ ጠበ​ቅ​ኋ​ቸ​ውም፤ የመ​ጽ​ሐ​ፉም ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ከጥ​ፋት ልጅ በቀር ከእ​ነ​ርሱ አንድ ስን​ኳን አል​ጠ​ፋም።


“በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ይገድሉአችሁማል፤ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።


ሴራ​ውም ከሶ​ር​ህያ ልጅ ከኢ​ዮ​አ​ብና ከካ​ህኑ ከአ​ብ​ያ​ታር ጋር ነበረ፤ እነ​ር​ሱም አዶ​ን​ያ​ስን ተከ​ት​ለው ይረ​ዱት ነበር።


ለእ​ር​ሱም “የአ​ባቴ የሳ​ኦል እጅ አታ​ገ​ኝ​ህ​ምና አት​ፍራ፤ አን​ተም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆ​ና​ለህ፤ እኔም ከአ​ንተ በታች እሆ​ና​ለሁ፤ ይህን ደግሞ አባቴ ሳኦል ያው​ቃል” አለው።


ዳዊ​ትም፥ “ስለ አባ​ትህ ስለ ዮና​ታን ቸር​ነት ፈጽሜ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለ​ሁና አት​ፍራ፤ የአ​ባ​ት​ህን አባት የሳ​ኦ​ልን መሬት ሁሉ እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም ሁል ጊዜ ከገ​በ​ታዬ እን​ጀ​ራን ትበ​ላ​ለህ” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements