Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 22:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ዳዊት አብ​ያ​ታ​ርን፦ ሶር​ያ​ዊው ዶይቅ በዚያ መኖ​ሩን ባየሁ ጊዜ፥ “ለሳ​ኦል በር​ግጥ ይነ​ግ​ራል ብዬ በዚያ ቀን አው​ቄ​ዋ​ለሁ፤ ለአ​ባ​ትህ ቤት ነፍስ ሁሉ ጥፋት በደ​ለ​ኛው እኔ ነኝ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ዳዊትም አብያታርን እንዲህ አለው፤ “ያን ዕለት ኤዶማዊው ዶይቅ እዚያ ስለ ነበር፣ ነገሩን በትክክል ለሳኦል እንደሚናገር ዐውቄአለሁ፤ ለመላው የአባትህ ቤተ ሰብ ዕልቂት ተጠያቂው እኔ ነኝ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ዳዊትም አብያታርን እንዲህ አለው፤ “ያን ዕለት ኤዶማዊው ዶይቅ እዚያ ስለ ነበር፥ ነገሩን በትክክል ለሳኦል እንደሚናገር አውቄአለሁ፤ ለመላው የአባትህ ቤተሰብ ዕልቂት ተጠያቂው እኔ ነኝ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ዳዊትም አብያታርን “እኔ በዚያ ቀን ኤዶማዊውን ዶይቅን እዚያ ባየሁት ጊዜ ሁሉን ነገር ለሳኦል እንደሚነግረው ዐውቄ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ስለ ዘመዶችህ ሁሉ እልቂት እኔ ተጠያቂነት አለብኝ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ዳዊት አብያታርን፦ ኤዶማዊው ዶይቅ በዚያ መኖሩን ባየሁ ጊዜ፦ ለሳኦል በእርግጥ ይነግራል ብዬ በዚያው ቀን አውቄዋለሁ፥ ለአባትህ ቤት ነፍስ ሁሉ የጥፋታቸው ምክንያት እኔ ነኝ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 22:22
3 Cross References  

አብ​ያ​ታ​ርም ሳኦል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ካህ​ናት እንደ ፈጀ ለዳ​ዊት ነገ​ረው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements