Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 20:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ዮና​ታ​ንም ለአ​ባቱ ለሳ​ኦል፥ “ስለ ምን ይሞ​ታል? ምንስ አደ​ረገ?” ብሎ መለ​ሰ​ለት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ዮናታንም፣ “ለምን ይገደላል? ጥፋቱስ ምንድን ነው?” ሲል አባቱን ጠየቀ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል “ስለምን ይሞታል? ምንስ አደረገ?” ሲል መለሰ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል “ስለምን ይሞታል? ምንስ አደረገ?” ሲል መለሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል፦ ስለ ምን ይሞታል? ያደረገውስ ምንድር ነው? ብሎ መለሰለት።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 20:32
17 Cross References  

ገዢውም “ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው?” አለ፤ እነርሱ ግን “ይሰቀል!” እያሉ ጩኸት አበዙ።


ነፍ​ሱ​ንም በእጁ ጥሎ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን ገደለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ርሱ ታላቅ መድ​ኀ​ኒት አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አይ​ተው ደስ አላ​ቸው፤ በከ​ንቱ ዳዊ​ትን ትገ​ድ​ለው ዘንድ ስለ​ምን በን​ጹሕ ደም ላይ ትበ​ድ​ላ​ለህ?”


ጲላ​ጦ​ስም ለሦ​ስ​ተኛ ጊዜ፥ “ምን ክፉ ነገር አደ​ረገ? እነሆ፥ ለሞት የሚ​ያ​በቃ ምክ​ን​ያት አላ​ገ​ኘ​ሁ​በ​ትም፤ እን​ኪ​ያስ ልግ​ረ​ፈ​ውና ልተ​ወው” አላ​ቸው።


ያዕ​ቆ​ብም ተቈጣ፤ ላባ​ንም ወቀ​ሰው፤ ያዕ​ቆ​ብም መለሰ፤ ላባ​ንም እን​ዲህ አለው፥ “የበ​ደ​ል​ሁህ በደል ምን​ድን ነው? ኀጢ​አ​ቴስ ምን​ድን ነው? ይህን ያህል ያሳ​ደ​ድ​ኸኝ?


“ሕጋ​ችን አስ​ቀ​ድሞ ሳይ​ሰማ፤ የሠ​ራ​ው​ንም ሳያ​ውቅ በሰው ይፈ​ር​ዳ​ልን?”


“የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ጥልቅ ነው፤ ማንስ ያው​ቀ​ዋል?


ከፀ​ሓይ በታች የተ​ደ​ረ​ገው ክፉ ሁሉ ለሁሉ ነው፤ የሁሉ ድርሻ አንድ ነውና። ደግ​ሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋ​ትን ትሞ​ላ​ለች፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ሳሉ ሁከት በል​ባ​ቸው አለ፥ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሙታን ይወ​ር​ዳሉ።


በመ​ን​ፈ​ስህ ለቍጣ ችኩል አት​ሁን፥ ቍጣ በሰ​ነ​ፎች ብብት ያር​ፋ​ልና።


ከቍጡ ሰው ጋር ባልንጀራ አትሁን፥ ከነዝናዛም ጓደኛ ጋር አትኑር።


እር​ሱም፦ መል​ካም ነው ቢል ለእኔ ለባ​ሪ​ያህ ሰላም ይሆ​ናል፤ ቢቈጣ ግን ክፋት ከእ​ርሱ ዘንድ በእኔ ላይ እንደ ተቈ​ረ​ጠች ዕወቅ።


ሳኦ​ልም፥ “ዳዊ​ትን ከግ​ንቡ ጋር አጣ​ብቄ እመ​ታ​ዋ​ለሁ” ብሎ ጦሩን ወረ​ወረ። ዳዊ​ትም ሁለት ጊዜ ከፊቱ ዘወር አለ።


ዮና​ታ​ንም ለአ​ባቱ ለሳ​ኦል ስለ ዳዊት መል​ካም ተና​ገረ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እርሱ አል​በ​ደ​ለ​ህ​ምና፥ ሥራ​ውም ለአ​ንተ እጅግ መል​ካም ሆኖ​አ​ልና ንጉሡ ባሪ​ያ​ውን ዳዊ​ትን አይ​በ​ድ​ለው፤


አቤ​ሜ​ሌ​ክም መልሶ ንጉ​ሡን፥ “ከባ​ሪ​ያ​ዎቹ ሁሉ የታ​መነ፥ ለን​ጉ​ሥም አማች የሆነ፥ የት​እ​ዛ​ዝህ ሁሉ አለቃ፥ በቤ​ት​ህም የከ​በረ እንደ ዳዊት ያለ ማን ነው?


ዳዊ​ትም ከአ​ው​ቴ​ዘ​ራማ ሸሸ፤ ወደ ዮና​ታ​ንም መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ምን አደ​ረ​ግሁ? ምንስ በደ​ልሁ? ነፍ​ሴ​ንም ይሻት ዘንድ በአ​ባ​ትህ ፊት ጥፋ​ቴና ኀጢ​አቴ ምን​ድን ነው?”


Follow us:

Advertisements


Advertisements