Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 20:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ዳዊ​ትም ዮና​ታ​ንን፥ “አባ​ትህ ስለ እኔ ክፉ ነገር የነ​ገ​ረህ እንደ ሆነ ማን ይነ​ግ​ረ​ኛል?” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ዳዊትም፣ “አባትህ ክፉ ቃል ቢመልስልህ ማን ይነግረኛል?” ብሎ ጠየቀው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ዳዊትም፥ “አባትህ ክፉ ቃል ቢመልስልህ ማን ይነግረኛል?” ብሎ ጠየቀው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ዳዊትም “ታዲያ አባትህ ስለ እኔ ክፉ ቃል ቢናገር ማን ያስረዳኛል?” ሲል ጠየቀ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ዳዊትም ዮናታንን፦ አባትህ ስለ እኔ ክፉ ነገር የነገረህ እንደ ሆን ማን ይነግረኛል? አለው።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 20:10
10 Cross References  

ንጉ​ሡም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች የመ​ከ​ሩ​ትን ምክር ትቶ ለሕ​ዝቡ ጽኑ ምላሽ መለ​ሰ​ላ​ቸው።


ስለ​ዚ​ህም በጌ​ታ​ች​ንና በቤቱ ሁላ ክፉ ነገር እን​ዲ​መጣ ተቈ​ር​ጦ​አ​ልና፥ እርሱ ክፉ ሰው ስለ ሆነ ማንም ሊና​ገ​ረው አይ​ች​ል​ምና የም​ታ​ደ​ር​ጊ​ውን ተመ​ል​ከ​ቺና ዕወቂ።”


ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንዱ ለና​ባል ሚስት ለአ​ቤ​ግያ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ራት፥ “እነሆ፥ ዳዊት በም​ድረ በዳ ሳለ ጌታ​ች​ንን ሰላም ሊሉት መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እርሱ ግን ፊቱን አዞ​ረ​ባ​ቸው።


ናባ​ልም ተነ​ሥቶ ለዳ​ዊት ብላ​ቴ​ኖች መለ​ሰ​ላ​ቸው እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ዳዊት ማን ነው? የእ​ሴ​ይስ ልጅ ማን ነው? እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከጌ​ቶ​ቻ​ቸው የኰ​በ​ለሉ አገ​ል​ጋ​ዮች ዛሬ ብዙ ናቸው።


“የሀ​ገሩ ጌታ የሆ​ነው ሰው በክፉ ንግ​ግር ተና​ገ​ረን፤ የም​ድ​ሪ​ቱም ሰላ​ዮች እን​ደ​ሆን አድ​ርጎ ወደ እስር ቤት አስ​ገ​ባን።”


ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን በአ​ያ​ቸው ጊዜ ዐወ​ቃ​ቸው፤ እን​ደ​ማ​ያ​ው​ቃ​ቸ​ውም ሆነ፤ ክፉ ቃል​ንም ተና​ገ​ራ​ቸው፥ “እና​ንተ ከወ​ዴት መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “ከከ​ነ​ዓን ምድር እህል ልን​ሸ​ምት የመ​ጣን ነን” አሉት።


ዮና​ታ​ንም፥ “ይህ ከአ​ንተ ይራቅ፤ ከአ​ባቴ ዘንድ ክፋት በላ​ይህ እንደ ተቈ​ረ​ጠች ያወ​ቅሁ እንደ ሆነ በከ​ተማ ባት​ኖ​ርም እን​ኳን ወደ አንተ መጥቼ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” አለው።


ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን፥ “ና፤ ወደ ሜዳ እን​ውጣ” አለው። ሁለ​ቱም ወደ ሜዳ ወጡ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements