Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የሚ​ሠ​ዋ​ውም ሰው፥ “አስ​ቀ​ድሞ እንደ ሕጉ ስቡ ይጢስ፤ ኋላም ሰው​ነ​ት​ህን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኛ​ትን ትወ​ስ​ዳ​ለህ” ቢለው፥ እርሱ፥ “አይ​ሆ​ንም፥ ነገር ግን አሁን ስጠኝ፤ ካል​ሆ​ነም በግድ አወ​ስ​ደ​ዋ​ለሁ” ይለው ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ሰውየውም፣ “በመጀመሪያ ሥቡ ይቃጠል፤ ከዚያ በኋላ የምትፈልገውን ትወስዳለህ” ቢለው እንኳ አገልጋዩ፣ “አይሆንም፤ አሁኑኑ ስጠኝ፤ አለዚያ በግድ እወስዳለሁ” ይለው ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ሰውየውም፦ “አስቀድሞ ስቡን ያቃጥሉት፥ ከዚያም በኋላ ሰውነትህ ደስ የሚያሰኛትን ያህል ትወስዳለህ” ቢለው፥ እርሱ፦ “አይሆንም፥ አሁን ልትሰጠኝ ይገባል፤ ካልሆነ ግን በግድ እወስዳለሁ!” ይለው ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሰውየውም “በመጀመሪያ ስቡን ያቃጥሉትና ከዚያ በኋላ የፈለግኸውን ትወስዳለህ” ቢለው፥ የካህኑ አገልጋይ “አይሆንም! አሁኑኑ ስጠኝ! እምቢ ብትል ግን በግድ እወስዳለሁ!” ይለው ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ሰውዮውም፦ አስቀድሞ ስቡን ያቃጥሉት ኋላም ሰውነትህ ደስ የሚያሰኛትን ትወስዳለህ ቢለው፥ እርሱ፦ አይሆንም፥ ነገር ግን አሁን ስጠኝ፥ እንቢም ብትል በግድ እወስደዋለሁ ይለው ነበር።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 2:16
9 Cross References  

ካህ​ኑም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው። ስቡ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት እንዲህ ይላል፥ በጥርሳቸው ሲነክሱ በሰላም ይሰብካሉ፥ በአፋቸው ግን አንዳች በማይሰጥ ሰው ላይ ሰልፍን ያስቡበታል።


ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው የነ​በ​ሩት አለ​ቆች ግን በሕ​ዝቡ ላይ አክ​ብ​ደው ነበር፤ ስለ እን​ጀ​ራ​ውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወ​ስዱ ነበር፤ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ በሕ​ዝቡ ላይ ይሰ​ለ​ጥኑ ነበር። እኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ፈራሁ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ግ​ሁም።


የዳ​ንም ልጆች እን​ዲህ አሉት፥ “የተ​ቈጡ ሰዎች እን​ዳ​ያ​ገ​ኙ​ህና ነፍ​ስ​ህም፥ የቤተ ሰቦ​ች​ህም ነፍስ እን​ዳ​ይ​ጠ​ፋ​ብህ፥ ድም​ፅህ በእኛ መካ​ከል አይ​ሰማ።”


ደግ​ሞም ስቡ ሳይ​ጤስ የካ​ህኑ ልጅ መጥቶ የሚ​ሠ​ዋ​ውን ሰው፥ “ጥሬ​ውን እንጂ የተ​ቀ​ቀ​ለ​ውን ሥጋ ከአ​ንተ አይ​ወ​ስ​ድ​ምና እጠ​ብ​ስ​ለት ዘንድ ለካ​ህኑ ሥጋ ስጠኝ” ይለው ነበር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቍር​ባን ይንቁ ነበ​ርና የዔሊ ልጆች ኀጢ​አት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጅግ ታላቅ ነበ​ረች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements