Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 2:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ደግ​ሞም ስቡ ሳይ​ጤስ የካ​ህኑ ልጅ መጥቶ የሚ​ሠ​ዋ​ውን ሰው፥ “ጥሬ​ውን እንጂ የተ​ቀ​ቀ​ለ​ውን ሥጋ ከአ​ንተ አይ​ወ​ስ​ድ​ምና እጠ​ብ​ስ​ለት ዘንድ ለካ​ህኑ ሥጋ ስጠኝ” ይለው ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ነገር ግን ሥቡ ገና ከመቃጠሉ በፊት የካህኑ አገልጋይ መጥቶ መሥዋዕት የሚያቀርበውን ሰው፣ “ካህኑ ጥሬውን እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ ስለማይቀበል፣ ለካህኑ የሚጠበስ ሥጋ ስጠኝ” ይለው ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከዚህም ሌላ፥ ስቡን ሳያቃጥሉ የካህኑ አገልጋይ መጥቶ የሚሠዋውን ሰው፦ “ጥሬውን እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ አይወስድምና እጠብስለት ዘንድ ለካህኑ ሥጋ ስጠኝ” ይለው ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከዚህም በቀር ጮማው ከመቃጠሉ በፊት የካህኑ አገልጋይ መሥዋዕቱን ወደሚሠዋው ሰው መጥቶ “ካህኑ ያንተን የተቀቀለ ሥጋ ሳይሆን ጥሬ ሥጋ ስለሚፈልግ ለእርሱ እንድጠብስለት ሥጋ ስጠኝ” ይለው ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ደግሞም ስቡን ሳያቃጥሉ የካህኑ ሎሌ መጥቶ የሚሠዋውን ሰው፦ ጥሬውን እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ አይወስድምና እጠብስለት ዘንድ ለካህኑ ሥጋ ስጠኝ ይለው ነበር።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 2:15
8 Cross References  

ካህ​ኑም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው። ስቡ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


እነ​ዚ​ህም ፍጻ​ሜ​ያ​ቸው ለጥ​ፋት የሆነ፥ ሆዳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​መ​ልኩ፥ ክብ​ራ​ቸ​ውም ውር​ደት የሆ​ነ​ባ​ቸው፥ ምድ​ራ​ዊ​ዉ​ንም የሚ​ያ​ስቡ ናቸው።


እነ​ርሱ ለጌ​ታ​ችን ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያይ​ደለ ለሆ​ዳ​ቸው ይገ​ዛ​ሉና፤ በነ​ገር ማታ​ለ​ልና በማ​ለ​ዛ​ዘ​ብም የብ​ዙ​ዎች የዋ​ሃ​ንን ልብ ያስ​ታሉ፤


እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውሃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥


ጥሬ​ው​ንም፥ በው​ኃም የበ​ሰ​ለ​ውን አት​ብሉ፤ ነገር ግን በእ​ሳት የተ​ጠ​በ​ሰ​ውን ራሱን፥ እግ​ሩ​ንና ሆድ ዕቃ​ውን ብሉት።


ወደ ድስ​ቱም ወይም ወደ ምን​ቸቱ ወይም ወደ አፍ​ላሉ ወይም ወደ ቶፋው ይሰ​ድ​ደው ነበር። ሜን​ጦ​ውም ያወ​ጣ​ውን ሁሉ ካህኑ ለእ​ርሱ ይወ​ስ​ደው ነበር፤ በሴ​ሎም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊሠዉ በሚ​ወጡ በእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ሁሉ ላይ እን​ዲህ ያደ​ርጉ ነበር።


የሚ​ሠ​ዋ​ውም ሰው፥ “አስ​ቀ​ድሞ እንደ ሕጉ ስቡ ይጢስ፤ ኋላም ሰው​ነ​ት​ህን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኛ​ትን ትወ​ስ​ዳ​ለህ” ቢለው፥ እርሱ፥ “አይ​ሆ​ንም፥ ነገር ግን አሁን ስጠኝ፤ ካል​ሆ​ነም በግድ አወ​ስ​ደ​ዋ​ለሁ” ይለው ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements