Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 16:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በመጡ ጊዜ ወደ ኤል​ያብ ተመ​ል​ክቶ፥ “በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ባው በፊቱ ነው” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እዚያ በደረሱ ጊዜም፣ ሳሙኤል ኤልያብን አይቶ፣ “በርግጥ እግዚአብሔር የቀባው ሰው እነሆ፤ በእግዚአብሔር ፊት ቆሟል” ብሎ ዐሰበ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እዚያ በደረሱ ጊዜም፥ ሳሙኤል ኤልያብን አይቶ፥ “በእርግጥ ጌታ የቀባው ሰው እነሆ፤ በጌታ ፊት ቆሞአል” ብሎ አሰበ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እዚያም በደረሱ ጊዜ ሳሙኤል ኤሊአብ ተብሎ የሚጠራውን የእሴይን ልጅ አይቶ “በእግዚአብሔር ፊት የቆመው ይህ ሰው በእርግጥ ለንጉሥነት የተመረጠ ነው” ሲል አሰበ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እንዲህም ሆነ፥ በመጡ ጊዜ ወደ ኤልያብ ተመልክቶ፦ በእውነት እግዚአብሔር የሚቀባው በፊቱ ነው አለ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 16:6
10 Cross References  

የእ​ሴ​ይም ሦስቱ ታላ​ላ​ቆች ልጆቹ ሳኦ​ልን ተከ​ት​ለው ወደ ሰልፉ ሄደው ነበር፤ ወደ ሰል​ፉም የሄ​ዱት የሦ​ስቱ ልጆች ስም ይህ ነበረ፤ ታላቁ ኤል​ያብ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም አሚ​ና​ዳብ፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ሣማዕ ነበረ።


እሴ​ይም የበ​ኵር ልጁን ኤል​ያ​ብን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም አሚ​ና​ዳ​ብን፥ ሦስ​ተ​ኛ​ው​ንም ሣማን፥


ዳዊ​ትም ዕቃ​ውን በዕቃ ጠባ​ቂው እጅ አኖ​ረው፤ ወደ​ሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ሮጦ ሄደ፤ የወ​ን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ደኅ​ን​ነት ጠየቀ።


ዛብ​ሄ​ል​ንና ስል​ማ​ናን፥ “በታ​ቦር የገ​ደ​ላ​ች​ኋ​ቸው ሰዎች እን​ዴት ያሉ ነበሩ?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “እን​ዳ​ንተ ያሉ ነበሩ፤ አን​ተ​ንም ይመ​ስሉ ነበር፤ መል​ካ​ቸ​ውም እንደ ነገ​ሥት ልጆች መልክ ነበረ” ብለው መለ​ሱ​ለት።


በይ​ሁዳ ወገን ላይ ከዳ​ዊት ወን​ድ​ሞች ኤል​ያብ፤ በይ​ሳ​ኮር ወገን ላይ የሚ​ካ​ኤል ልጅ ዖምሪ፤


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በልቡ አለ፥ “እነሆ፥ ዛሬ መን​ግ​ሥት ወደ ዳዊት ቤት ይመ​ለ​ሳል።


ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ የዘ​ለ​ዓ​ለም ንጉሥ እሆን ዘንድ ከአ​ባቴ ቤት ሁሉ መር​ጦ​ኛል፤ ይሁ​ዳ​ንም አለቃ ይሆን ዘንድ መር​ጦ​ታል፤ ከይ​ሁ​ዳም ቤት የአ​ባ​ቴን ቤት መር​ጦ​አል፤ ከአ​ባ​ቴም ልጆች መካ​ከል በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ያነ​ግ​ሠኝ ዘንድ እኔን ሊመ​ር​ጠኝ ወደደ።


ሮብ​ዓ​ምም የዳ​ዊ​ትን ልጅ የኢ​ያ​ሪ​ሙ​ትን ሴት ልጅ ሞላ​ትን አገባ፤ እና​ቷም የእ​ሴይ ልጅ የኤ​ል​ያብ ልጅ አቢ​ካ​ኤል ነበ​ረች።


ነገር ግን ክብር በም​ድ​ራ​ችን ያድር ዘንድ ማዳኑ ለሚ​ፈ​ሩት ቅርብ ነው።


በዶር ሀገር ዳርቻ ሁሉ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነበረ፤ ለእ​ር​ሱም የሰ​ሎ​ሞን ልጅ ጣፈ​ትም ሚስቱ ነበ​ረች፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements