Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 16:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሳኦ​ልም ወደ እሴይ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልኮ፥ “ከመ​ን​ጋ​ዎ​ችህ ጋር ያለ​ውን ልጅ​ህን ዳዊ​ትን ላክ​ልኝ” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከዚያም ሳኦል፣ “ከበጎች ጋራ ያለውን ልጅህን ዳዊትን ላክልኝ” ሲል መልክተኞችን ወደ እሴይ ላከ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ከዚያም ሳኦል፥ “ከበጎች ጋር ያለውን ልጅህን ዳዊትን ላክልኝ” ሲል መልክተኞችን ወደ እሴይ ላከ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ስለዚህም ሳኦል ወደ እሴይ መልእክተኞች ልኮ “የበጎች እረኛ የሆነውን ልጅህን ዳዊትን ላክልኝ” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ሳኦልም ወደ እሴይ መልክተኞች ልኮ፦ ከበጎች ጋር ያለውን ልጅህን ዳዊትን ላክልኝ አለ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 16:19
12 Cross References  

ዳዊ​ትም የአ​ባ​ቱን በጎች ለመ​ጠ​በቅ ከሳ​ኦል ዘንድ ወደ ቤተ ልሔም ይመ​ላ​ለስ ነበር።


ሳሙ​ኤ​ልም እሴ​ይን፥ “ልጆ​ችህ እኒህ ብቻ ናቸው?” አለው። እር​ሱም፥ “ታናሹ ገና ቀር​ቶ​አል፤ እነ​ሆም፥ በጎ​ችን ይጠ​ብ​ቃል” አለ። ሳሙ​ኤ​ልም እሴ​ይን፥ “እርሱ እስ​ኪ​መጣ ድረስ ለማ​ዕድ አን​ቀ​መ​ጥ​ምና ልከህ አስ​መ​ጣው” አለው።


በቴ​ቁሔ በላም ጠባ​ቂ​ዎች መካ​ከል የነ​በረ አሞጽ በይ​ሁዳ ንጉሥ በዖ​ዝ​ያን ዘመን፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በዮ​አስ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ዘመን፥ የም​ድር መና​ወጥ ከሆ​ነ​በት ከሁ​ለት ዓመት በፊት ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያየው ቃል ይህ ነው።


ዐለ​ቱን ወደ ውኃ ምንጭ፥ ባል​ጭ​ቱ​ንም ወደ ውኃ ኩሬ የለ​ወጠ።


ከዚ​ያም ሄደ፤ የሣ​ፋ​ጥ​ንም ልጅ ኤል​ሳ​ዕን በዐ​ሥራ ሁለት ጥማድ በሬ​ዎች ሲያ​ርስ፥ እር​ሱም ከዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ጋር ሆኖ አገ​ኘው። ኤል​ያ​ስም ወደ እርሱ አልፎ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ውን ጣለ​በት።


ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንዱ መልሶ፥ “እነሆ፥ መል​ካም አድ​ርጎ በገና ሲመታ የቤተ ልሔ​ሙን የእ​ሴ​ይን ልጅ አይ​ቻ​ለሁ፤ ሰው​የ​ውም ጠቢብ፥ ተዋ​ጊም ነው፤ በነ​ገ​ርም ብልህ፥ መል​ኩም ያማረ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነው” አለ።


እሴ​ይም እን​ጀ​ራና የወ​ይን ጠጅ አቁ​ማዳ የተ​ጫነ አህያ፥ አን​ድም የፍ​የል ጠቦት ወስዶ በልጁ በዳ​ዊት እጅ ወደ ሳኦል ላከ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements