1 ሳሙኤል 16:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ልኮም አስመጣው፤ እርሱም ቀይ፥ ዐይኑም የተዋበ፥ መልኩም ያማረ ነበረ። እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “ይህ መልካም ነውና ተነሥተህ ዳዊትን ቅባው” አለው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ስለዚህ ልኮ አስመጣው፤ እርሱም ደም ግባት ያለው፣ ዐይኑ የሚያምርና መልከ መልካም ነበረ። እግዚአብሔርም፣ “የመረጥሁት ይህ ነውና ተነሥተህ ቀባው” አለው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ስለዚህ ልኮ አስመጣው፤ እርሱም ደም ግባት ያለው፥ ዐይኑ የሚያምርና መልከ መልካም ነበረ። ጌታም፥ “የመረጥሁት ይህ ነውና ተነሥተህ ቀባው” አለው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ስለዚህም እሴይ ልኮ አስጠራው፤ እርሱ ቀይ፥ መልከ መልካምና ዐይኖቹ የሚያበሩ ጤናማ ወጣት ነበር፤ እግዚአብሔርም ሳሙኤልን “የመረጥኩት ሰው ይህ ነውና ተነሥተህ እርሱን ቀባው!” አለው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ልኮም አስመጣው፥ እርሱም ቀይ፥ ዓይኑም የተዋበ፥ መልኩም ያማረ ነበረ። እግዚአብሔርም፦ ይህ ነውና ተነሥተህ ቅባው አለ። See the chapter |