Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 15:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ሄደህ ኀጢ​ኣ​ተ​ኞ​ቹን አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ፈጽ​መህ አጥ​ፋ​ቸው፤ እስ​ኪ​ጠ​ፉም ድረስ ውጋ​ቸው ብሎ በመ​ን​ገድ ላከህ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እግዚአብሔርም፣ ‘ሄደህ እነዚያን ኀጢአተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው፤ ጨርሰህ እስክታጠፋቸውም ድረስ ውጋቸው’ ብሎ ልኮህ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ጌታም፥ ‘ሄደህ ኃጢአተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው፥ እስኪጠፉም ድረስ ውጋቸው’ ብሎ ልኮህ ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ኃጢአተኞች የሆኑትን እነዚያን አማሌቃውያንን እንድትደመስስ ልኮሃል፤ እስኪጠፉም ድረስ እነርሱን ግደል ብሎ ነግሮሃል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እግዚአብሔርም፦ ሄደህ ኃጢአተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው፥ እስኪጠፉም ድረስ ውጋቸው ብሎ በመንገድ ላከህ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 15:18
9 Cross References  

እግዚአብሔርን መፍራት ለደግ ሰው ብርታት ነው፥ ጥፋት ግን ክፋት ለሚያደርጉ ነው።


ሞት ለዐ​መ​ፀኛ፥ መለ​የ​ትም ኀጢ​አ​ትን ለሚ​ሠሩ ነው።


የእ​ነ​ዚህ ኃጥ​ኣን ጥና​ዎ​ቻ​ቸው በሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ጥፋት ተቀ​ድ​ሰ​ዋ​ልና፤ የተ​ጠ​ፈ​ጠፈ ሰሌዳ አድ​ር​ጋ​ቸው፤ ለመ​ሠ​ዊያ መለ​በ​ጫም ይሁኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቅ​ር​በ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና የተ​ቀ​ደሱ ናቸው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ምል​ክት ይሆ​ናሉ።”


በአ​ራ​ተ​ኛው ትው​ልድ ግን ወደ​ዚህ ይመ​ለ​ሳሉ፤ እስከ ዛሬ ድረስ የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ኀጢ​አት አል​ተ​ፈ​ጸ​መ​ምና።”


የሰ​ዶም ሰዎች ግን ክፉ​ዎ​ችና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጅግ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ነበሩ።


በደለኞችን ክፉ ነገር ይከተላቸዋል፤ ጻድቃንን ግን መልካም ነገር ያገኛቸዋል።


እኛ በት​ው​ል​ዳ​ችን አይ​ሁድ ነን፤ ኀጢ​አ​ተ​ኞች የሆኑ አሕ​ዛ​ብም አይ​ደ​ለ​ንም።


ተመ​ል​ሰ​ውም ቃዴስ ወደ ተባ​ለች ወደ ፍርድ ምንጭ መጡ፤ የአ​ማ​ሌ​ቅን አለ​ቆች ሁሉና በአ​ሳ​ሶን ታማር የሚ​ኖሩ አሞ​ራ​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ሉ​አ​ቸው።


አሁ​ንም ሄደህ አማ​ሌ​ቅ​ንና ኢያ​ሬ​ምን ምታ፤ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ፈጽ​መህ አጥፋ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የም​ታ​ድ​ነው የለም። አጥ​ፋ​ቸው፤ መከ​ራም አጽ​ና​ባ​ቸው፤ የእ​ነ​ርሱ የሆ​ነ​ውን ሁሉ አጥፋ፤ ለያ​ቸ​ውም፤ አት​ማ​ራ​ቸ​ውም፤ ወን​ዱ​ንና ሴቱን፥ ብላ​ቴ​ና​ው​ንና ሕፃ​ኑን፥ በሬ​ው​ንና በጉን፥ ግመ​ሉ​ንና አህ​ያ​ውን ግደል።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements