1 ሳሙኤል 15:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ሳሙኤልም ሳኦልን አለው፥ “በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን እቀባህ ዘንድ እግዚአብሔር ላከኝ፤ አሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ስማ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ቀብቼ እንዳነግሥህ፣ እግዚአብሔር የላከው እኔን ነው፤ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ድምፅ አሁን ስማ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን እንድቀባህ ጌታ ላከኝ፤ አሁንም የጌታን ቃል ስማ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ቀብቼ እንዳነግሥህ እግዚአብሔር የላከኝ እኔ ነኝ፤ አሁንም ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር የሚለውን ስማ፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ሳሙኤልም ሳኦልን አለው፦ በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን እቀባህ ዘንድ እግዚአብሔር ላከኝ፥ አሁንም የእግዚአብሔርን ድምፅ ስማ። See the chapter |