Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 14:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ዮና​ታ​ንም ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር ሊሻ​ገ​ር​በት በወ​ደ​ደው መተ​ላ​ለ​ፊያ መካ​ከል በወ​ዲህ አንድ ሾጣጣ፥ በወ​ዲ​ህም አንድ ሾጣጣ ድን​ጋ​ዮች ነበሩ፤ የአ​ን​ዱም ስም ባዚስ፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም ሴና ነበረ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ዮናታን ወደ ፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር ለመሻገር በፈለገበት መተላለፊያ ግራና ቀኝ አንዱ ቦጼጽ ሌላው ሴኔ የተባሉ ሁለት ሾጣጣ ዐለቶች ነበሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ዮናታን ወደ ፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር ለመሻገር በፈለገበት መተላለፊያ ግራና ቀኝ ሁለት ሾጣጣ ድንጋዮች ነበሩ፤ የአንዱ ስም ቦጼጽ ሲሆን፥ ሌላው ሴኔ ተብሎ ይጠራል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ዮናታን ወደ ፍልስጥኤማውያን ሰፈር ለመድረስ በሚክማስ መተላለፊያ መውጣት ነበረበት፤ በመተላለፊያውም ከግራና ከቀኝ ሁለት ሾጣጣ አለቶች ሲኖሩ የአንደኛው አለት ስም ቦጼጽ፥ የሁለተኛውም ስም ሴኔ ተብሎ ይጠራል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ዮናታንም ወደ ፍልስጥኤማውያን ጭፍራ ሊሻገርበት በወደደው መተላለፊያ መካከል በወዲህ አንድ ሾጣጣ በወዲህ አንድ ሾጣጣ ድንጋዮች ነበሩ፥ የአንዱም ስም ቦጼጽ የሁለተኛውም ስም ሴኔ ነበረ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 14:4
3 Cross References  

ከዚ​ያም ጥቂ​ቶች ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር ወደ ማኪ​ማስ መተ​ላ​ለ​ፊያ ወጡ።


አን​ደ​ኛዋ መን​ገድ በማ​ኪ​ማስ አን​ጻር በመ​ስዕ በኩል የም​ት​መጣ ናት፤ ሁለ​ተ​ኛ​ዋም መን​ገድ በገ​ባ​ዖን አን​ጻር በአ​ዜብ በኩል የም​ት​መጣ ነበ​ረች።


በዓ​ለቱ ገደል ላይ ይኖ​ራል፤ በገ​ደሉ ገመ​ገ​ምና በጥጉ ያድ​ራል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements