Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 14:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 እስ​ራ​ኤ​ልን የሚ​ያ​ድን ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ኀጢ​ኣቱ በልጄ በዮ​ና​ታን ቢሆን ፈጽሞ ይሞ​ታል” አለ። ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ አንድ የመ​ለ​ሰ​ለት ሰው አል​ነ​በ​ረም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 እስራኤልን የታደገ ሕያው እግዚአብሔርን አድራጊው ልጄ ዮናታን እንኳ ቢሆን መሞት አለበት።” ነገር ግን ከሕዝቡ መካከል የመለሰለት አንድም አልነበረም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 እስራኤልን የታደገ ሕያው ጌታን! አድራጊው ልጄ ዮናታን እንኳ ቢሆን መሞት አለበት።” ነገር ግን ከሕዝቡ መካከል የመለሰለት አንድም አልነበረም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 በደል ሠርቶ የተገኘው ሰው ልጄ ዮናታን እንኳ ቢሆን በሞት እንደሚቀጣ ለእስራኤል ድልን በሰጠው በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ።” ነገር ግን አንዳች መልስ የሰጠው ሰው አልተገኘም።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 14:39
10 Cross References  

ዳዊ​ትም በዚያ ሰው ላይ ተቈጣ፤ ዳዊ​ትም ናታ​ንን፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ይህን ያደ​ረገ ሰው ሞት የሚ​ገ​ባው ነው።


ሳኦ​ልም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ያድ​ር​ግ​ብኝ፤ እን​ዲ​ህም ይጨ​ም​ር​ብኝ፤ ዛሬ ፈጽ​መህ ትሞ​ታ​ለህ” አለ።


ሳኦ​ልም በዚያ ቀን ትልቅ በደል ፈጸመ፤ “ጠላ​ቶቼን እስ​ክ​በ​ቀል እስከ ማታ ድረስ መብል የሚ​በላ ሰው ርጉም ይሁን” ብሎ ሕዝ​ቡን አም​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና። ሕዝ​ቡም ሁሉ እህል አል​ቀ​መ​ሱም። ሀገ​ሩም ሁሉ ምሳ አል​በ​ላም።


በሁ​ሉም ከን​ቱ​ነት አለ፥ የጻ​ድ​ቁና የበ​ደ​ለ​ኛው፥ የመ​ል​ካ​ሙና የክ​ፉው፥ የን​ጹ​ሑና የር​ኩሱ፥ መሥ​ዋ​ዕ​ትን የሚ​ሠ​ዋ​ውና የማ​ይ​ሠ​ዋው፥ የመ​ል​ካ​ሙና እን​ዲሁ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛው፥ የመ​ሐ​ላ​ኛ​ውና እን​ዲሁ መሐ​ላን የሚ​ፈ​ራው ድርሻ አንድ ነው።


ሳኦ​ልም ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በዚህ ነገር ክፉ አያ​ገ​ኝ​ሽም ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማለ​ላት።


ንጉ​ሡም፥ “አቤ​ሜ​ሌክ ሆይ! አን​ተና የአ​ባ​ትህ ቤት ሁሉ ፈጽ​ማ​ችሁ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ” አለ።


የእ​ሴይ ልጅ በም​ድር ላይ በሕ​ይ​ወት በሚ​ኖ​ር​በት ዘመን ሁሉ መን​ግ​ሥ​ትህ አት​ጸ​ናም፤ አሁ​ንም ሞት የሚ​ገ​ባው ነውና ያን ብላ​ቴና ያመ​ጡት ዘንድ ላክ” አለው።


ሳኦ​ልም የዮ​ና​ታ​ንን ቃል ሰማ፤ ሳኦ​ልም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዳዊት አይ​ገ​ደ​ልም” ብሎ ማለ።


እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሁሉ፥ “እና​ንተ አንድ ወገን ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እኔና ልጄ ዮና​ታ​ንም አንድ ወገን እን​ሆ​ና​ለን” አለ። ሕዝ​ቡም ሳኦ​ልን፥ “ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን አድ​ርግ” አሉት።


ንጉ​ሡም ኢዮ​አ​ብን፥ “እነሆ፥ ይህን ነገር አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ ሂድና ብላ​ቴ​ና​ውን አቤ​ሴ​ሎ​ምን መል​ሰው” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements