Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 14:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ሳኦ​ልም፥ “በሕ​ዝቡ መካ​ከል እየ​ዞ​ራ​ችሁ፦ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው በሬ​ው​ንና በጉን ወደ እኔ ያቅ​ርብ፥ በዚ​ህም እረ​ዱና ብሉ፤ ከደ​ሙም ጋር በመ​ብ​ላ​ታ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​በ​ድሉ” በሉ​አ​ቸው አለ። እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሰው ሁሉ በእጁ ያለ​ውን በዚ​ያች ሌሊት አቀ​ረበ፤ በዚ​ያም አረ​ደው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 እርሱም፣ “በሕዝቡ መካከል እየዞራችሁ፣ ‘እያንዳንዳችሁ በሬዎቻችሁንና በጎቻችሁን አምጡ፤ እዚሁ ዐርዳችሁ ብሉ፤ ነገር ግን ሥጋውን ከነደሙ በመብላት እግዚአብሔርን አትበድሉ’ በሏቸው” አለ። ስለዚህ በዚያች ሌሊት እያንዳንዱ ሰው በሬውን አምጥቶ በዚያ ዐረደው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ሳኦልም፥ “በሕዝቡ መካከል እየዞራችሁ፥ ‘እያንዳንዳችሁ በሬዎቻችሁንና በጎቻችሁን አምጡ፤ እዚሁ ዐርዳችሁ ብሉ፤ ነገር ግን ሥጋውን ከነደሙ በመብላት ጌታን አትበድሉ’ በሏቸው” አለ። ስለዚህ በዚያች ሌሊት እያንዳንዱ ሰው በሬውን አምጥቶ በዚያ አረደው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ከዚህም በኋላ ሌላ ትእዛዝ እንዲህ ሲል አስተላለፈ፤ “ወደ ሕዝቡ ሄዳችሁ ‘የቀንድ ከብቶቻችሁንና በጎቻችሁን ሁሉ አምጡ፤ እነርሱንም ዐርዳችሁ በዚህ ስፍራ መመገብ አለባችሁ፤ ደም ያለበትንም እርጥብ ሥጋ በመብላት በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት አትሥሩ’ ብላችሁ ንገሩአቸው።” ስለዚህም ሕዝቡ ሁሉ በዚያን ሌሊት የቀንድ ከብቶቻቸውንና በጎቻቸውን ሁሉ አምጥተው በዚያ ዐረዱ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ሳኦልም፦ በሕዝቡ መካከል እየዞራችሁ፦ እያንዳንዱ ሰው በሬውንና በጉን ወደ እኔ ያቅርብ፥ በዚህም እረዱና ብሉ፥ ከደሙም ጋር በመብላታችሁ እግዚአብሔርን አትበድሉ በሉአቸው አለ። እያንዳንዱም ሰው ሁሉ በእጁ ያለውን በሬውን በዚያች ሌሊት አቀረበ፥ በዚያም አረደው።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 14:34
3 Cross References  

ነገር ግን ደመ ነፍስ ያለ​በ​ትን ሥጋ አት​ብሉ፤


ለሳ​ኦ​ልም፥ “እነሆ፥ ሕዝቡ ከደሙ ጋር በመ​ብ​ላ​ታ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በደሉ” ብለው ነገ​ሩት። ሳኦ​ልም በጌ​ቴም “ትልቅ ድን​ጋይ አን​ከ​ባ​ል​ላ​ችሁ አቅ​ር​ቡ​ልኝ” አላ​ቸው።


ሳኦ​ልም በዚያ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊ​ያን ሠራ፤ ይኸ​ውም ሳኦል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሠ​ራው የመ​ጀ​መ​ሪያ መሠ​ዊያ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements