Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 14:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በዚ​ያም ቀን አኪያ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ኤፉድ ይለ​ብስ ነበ​ርና ሳኦል፥ “ኤፉ​ድን አምጣ” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሳኦልም አኪያን፣ “የእግዚአብሔርን ታቦት ወደዚህ አምጣ” አለው፤ በዚያ ጊዜ ታቦቱ በእስራኤላውያን ዘንድ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሳኦልም አኪያን፥ “የእግዚአብሔርን ታቦት ወደዚህ አምጣ” አለው፤ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ታቦት በእስራኤላውያን ዘንድ ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ሳኦልም ካህኑን አኪያን “ኤፉዱን ይዘህ ና” አለው። በዚያን ቀን ካህኑ አኪያ ኤፉድ ለብሶ በእስራኤል ሕዝብ ፊት ነበር፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በዚያም ቀን አኪያ በእስራኤል ልጆች ፊት ኤፉድ ለብሶ ነበርና ሳኦል፦ ኤፉድን አምጣ አለው።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 14:18
13 Cross References  

ኦር​ዮም ለዳ​ዊት፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦ​ትና እስ​ራ​ኤል፥ ይሁ​ዳም በድ​ን​ኳን ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ጌታዬ ኢዮ​አ​ብና የጌ​ታ​ዬም አገ​ል​ጋ​ዮች በሰፊ ሜዳ ሰፍ​ረ​ዋል፤ እኔ ልበ​ላና ልጠጣ ወይስ ከሚ​ስቴ ጋር ልተኛ ወደ ቤቴ እሄ​ዳ​ለ​ሁን? በሕ​ይ​ወ​ት​ህና በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ! ይህን ነገር አላ​ደ​ር​ገ​ውም” አለው።


የቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ሰዎ​ችም መጥ​ተው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት አወጡ፤ በኮ​ረ​ብ​ታ​ውም ላይ ወዳ​ለው ወደ አሚ​ና​ዳብ ቤት አገ​ቡ​አት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት እን​ዲ​ጠ​ብቅ ልጁን አል​ዓ​ዛ​ርን ቀደ​ሱት።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወስ​ደው ወደ ዳጎን ቤት አገ​ቡ​አት፤ በዳ​ጎ​ንም አጠ​ገብ አኖ​ሩ​አት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወጥ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ አለ​ቀሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር ለመ​ዋ​ጋት ዳግ​መኛ እን​ቀ​ር​ባ​ለን?” ብለው ጠየቁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም “በእ​ነ​ርሱ ላይ ውጡ” አለ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተነ​ሥ​ተው ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “የብ​ን​ያ​ምን ልጆች ለመ​ው​ጋት መሪ ሆኖ ማን ይው​ጣ​ልን?” ብለው ጠየ​ቁት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይሁዳ መሪ ይሁን” አለ፤


በካ​ህ​ኑም በአ​ል​ዓ​ዛር ፊት ይቁም፤ እር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ፍርድ ይጠ​ይ​ቅ​ለት፤ እርሱ ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፤ በቃ​ሉም ይግቡ።”


ሳኦ​ልም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ፥ “እስኪ ተቋ​ጠሩ፤ ከእኛ ዘንድ የሄደ ማን እንደ ሆነ ተመ​ል​ከቱ” አላ​ቸው። በተ​ቋ​ጠ​ሩም ጊዜ እነሆ፥ ዮና​ታ​ንና ጋሻ ጃግ​ሬው በዚያ አል​ተ​ገ​ኙም።


ሳኦ​ልም፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በሌ​ሊት ተከ​ት​ለን እን​ው​ረድ፤ እስ​ኪ​ነ​ጋም ድረስ እን​በ​ዝ​ብ​ዛ​ቸው፤ አንድ ሰው እንኳ አና​ስ​ቀ​ር​ላ​ቸው” አለ። እነ​ር​ሱም፥ “ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን ሁሉ አድ​ርግ” አሉት። ካህ​ኑም፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ቅ​ረብ” አለ።


ዳዊ​ትም ሳኦል በእ​ርሱ ለክ​ፋት ዝም እን​ደ​ማ​ይል ዐወቀ፤ ዳዊ​ትም ካህ​ኑን አብ​ያ​ታ​ርን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ኤፉድ ወደ​ዚህ አምጣ” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements