Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 13:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሳኦ​ልም፥ “የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት አም​ጡ​ልኝ” አለ። የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አሳ​ረገ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በዚህ ጊዜ ሳኦል፣ “የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕቱን አምጡልኝ” አለ። ከዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በዚህ ጊዜ ሳኦል፥ “የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕቱን አምጡልኝ” አለ። ከዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ስለዚህም ሳኦል ሕዝቡን “የሚቃጠለውንና ለደኅንነት የሚሆነውን የአንድነት መሥዋዕት አምጡልኝ” ብሎ በማዘዝ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረበ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሳኦልም፦ የሚቃጠል መሥዋዕትና የደኅንነት መሥዋዕት አምጡልኝ አለ።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 13:9
13 Cross References  

ገባ​ዖን ፈጽማ ትሰፋ ነበ​ርና በዚያ መሥ​ዋ​ዕት ይሠዋ ዘንድ ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ሰሎ​ሞ​ንም በዚያ መሠ​ዊያ ላይ በገ​ባ​ዖን አንድ ሺህ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ።


ወደ​ዚ​ያም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ቀዳ​ም​ያ​ታ​ች​ሁን፥ ስዕ​ለ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ በፈ​ቃ​ዳ​ችሁ የም​ታ​ቀ​ር​ቡ​ትን፥ የላ​ማ​ች​ሁ​ንና የበ​ጋ​ች​ሁ​ንም በኵ​ራት ውሰዱ።


በሬን የሚ​ሠ​ዋ​ልኝ ኃጥእ ውሻን እን​ደ​ሚ​ያ​ር​ድ​ልኝ ነው፤ የእ​ህ​ልን ቍር​ባን የሚ​ያ​ቀ​ር​ብም የእ​ሪ​ያን ደም እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ርብ ነው፤ ዕጣ​ን​ንም ለመ​ታ​ሰ​ቢያ የሚ​ያ​ጥን አም​ላ​ክን እን​ደ​ሚ​ፀ​ርፍ ነው፤ እነ​ዚህ የገዛ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን መረጡ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸው ደስ ይላ​ታል።


የኃጥኣን መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ በክፋት ያቀርቡታልና።


ጽድቅንና ቅን ፍርድን ማድረግ መሥዋዕት ከመሠዋት ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ነው።


ጠላቴን እበቀለዋለሁ አትበል፤ ነገር ግን እንዲረዳህ እግዚአብሔርን ተማመን።


የክፉዎች መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ ነው፤ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው።


ነፍሴ ስድ​ብን ጠግ​ባ​ለ​ችና፥ ለሥ​ጋ​ዬም ድኅ​ነ​ትን አጣሁ።


በዚ​ያም ዳዊት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረበ። ሰሎ​ሞ​ንም በኋላ ዘመን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመረ፤ ያን​ጊዜ አነ​ስ​ተኛ ነበ​ርና። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ሀገ​ሪቱ የተ​ለ​መ​ነ​ውን ሰማ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ተከ​ለ​ከለ።


በዚ​ያም ቀን አኪያ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ኤፉድ ይለ​ብስ ነበ​ርና ሳኦል፥ “ኤፉ​ድን አምጣ” አለው።


ነገር ግን አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ችሁ ሁሉ በአ​ንዱ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመ​ረ​ጠ​ውን ስፍራ ትሻ​ላ​ችሁ፤ ወደ​ዚ​ያም ትመ​ጣ​ላ​ችሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements