1 ሳሙኤል 12:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ሳሙኤልም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፥ እግዚአብሔርም በዚያ ቀን ነጐድጓድንና ዝናብን ላከ፤ ያንጊዜም ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርንና ሳሙኤልን እጅግ ፈሩአቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ከዚህ በኋላ ሳሙኤል ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ በዚያ ዕለት እግዚአብሔር ነጐድጓድና ዝናብ ላከ። ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርንና ሳሙኤልን እጅግ ፈሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ከዚህ በኋላ ሳሙኤል ወደ ጌታ ጮኸ፤ በዚያኑ ዕለት ጌታ ነጐድጓድና ዝናብ ላከ። ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ ጌታንና ሳሙኤልን እጅግ ፈሩ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ከዚህም በኋላ ሳሙኤል ጸለየ፤ እግዚአብሔርም በዚያኑ ዕለት ነጐድጓድና ዝናብ ላከ፤ ከዚህም የተነሣ ሕዝቡ እግዚአብሔርንና ሳሙኤልን እጅግ ፈሩ፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ሳሙኤልም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፥ እግዚአብሔርም በዚያን ቀን ነጎድጓድና ዝናብ ላከ፥ ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርንና ሳሙኤልን እጅግ ፈሩአቸው። See the chapter |