Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 12:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ብት​ፈሩ፥ ብታ​መ​ል​ኩ​ትም፥ ቃሉ​ንም ብት​ሰሙ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ላይ ባታ​ምፁ፥ እና​ን​ተና በእ​ና​ንተ ላይ የነ​ገ​ሠው ንጉሥ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ብት​ከ​ተሉ፥ መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እግዚአብሔርን የምትፈሩና የምታመልኩ፣ የምትታዘዙትና በትእዛዞቹ ላይ የማታምፁ ከሆነ፣ እንዲሁም እናንተና በእናንተ ላይ የነገሠው ንጉሥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ከተከተላችሁ መልካም ይሆንላችኋል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የምትፈሩና የምታመልኩ፥ የምትታዘዙትና በትእዛዛቱ ላይ የማታምጹ ከሆነ፥ እንዲሁም እናንተና በእናንተ ላይ የነገሠው ንጉሥ አምላካችሁን ጌታን ከተከተላችሁ፥ መልካም ይሆንላችኋል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እግዚአብሔርን ብትፈሩና ብታመልኩት፥ ቃሉንም ብታዳምጡ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ብትጠብቁ፥ እናንተና በእናንተ ላይ የነገሠው ንጉሥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ብትከተሉ ሁሉ ነገር ይሠምርላችኋል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እግዚአብሔርን ብትፈሩ ብታመልኩትም፥ ቃሉንም ብትሰሙ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ላይ ባታምፁ፥ እናንተና በእናንተ ላይ የነገሠው ንጉሥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ብትከተሉ፥ መልካም ይሆንላችኋል።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 12:14
11 Cross References  

“አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩት፤ በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ን​ነ​ትም አም​ል​ኩት፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በወ​ንዝ ማዶ፥ በግ​ብ​ፅም ውስጥ ያመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት ከእ​ና​ንተ አርቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አም​ልኩ።


ክፉ ምክ​ርን መክ​ረ​ዋ​ልና ለነ​ፍ​ሳ​ቸው ወዮ​ላት! እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ጻድ​ቁን እን​ሻ​ረው፤ ሸክም ሆኖ​ብ​ና​ልና፤” ስለ​ዚህ የእ​ጃ​ቸ​ውን ሥራ ፍሬ ይበ​ላሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትታ​ችሁ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ብታ​መ​ልኩ፥ መል​ካ​ምን ባደ​ረ​ገ​ላ​ችሁ ፋንታ ተመ​ልሶ ክፉ ነገር ያደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋል፤ ያጠ​ፋ​ች​ሁ​ማል” አላ​ቸው።


በበጎ ምግ​ባር ጸን​ተው ለሚ​ታ​ገሡ፥ ምስ​ጋ​ናና ክብ​ርን፥ የማ​ይ​ጠፋ ሕይ​ወ​ት​ንም ለሚሹ እርሱ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል።


ጻዴ። ቃሉን አማ​ር​ሬ​አ​ለ​ሁና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነው። እና​ንተ አሕ​ዛብ ሁሉ እባ​ካ​ችሁ ስሙ፤ መከ​ራ​ዬ​ንም ተመ​ል​ከቱ፤ ደና​ግ​ሎ​ችና ጐል​ማ​ሶች ተማ​ር​ከው ሄደ​ዋ​ልና።


ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ችሁ፥ ከባ​ር​ነ​ትም ቤት ካዳ​ና​ችሁ ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ስ​ታ​ችሁ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትሄ​ድ​ባት ዘንድ ካዘ​ዘህ መን​ገድ ሊያ​ወ​ጣህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገ​ደል፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከአ​ንተ አርቅ።


እር​ሱም ንጉ​ሡን አሳን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንና የብ​ን​ያ​ምን ሕዝብ ሁሉ ሊገ​ናኝ ወጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አሳ ይሁ​ዳና ብን​ያም ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤ እና​ንተ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ብት​ሆኑ እርሱ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ ብት​ፈ​ል​ጉ​ትም ይገ​ኝ​ላ​ች​ኋል፤ ብት​ተ​ዉት ግን ይተ​ዋ​ች​ኋል።


በብ​ዔል ፌጎ​ርም ዐለቁ፥ የሞተ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም በሉ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements