1 ሳሙኤል 10:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ከዚያም ስፍራ ያለ አንድ ሰው፥ “አባቱስ ማን ነው?” ብሎ መለሰ። ስለዚህም “ሳኦል ደግሞ ከነቢያት ወገን ነውን?” የሚል ምሳሌ ሆነ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 በዚያ ነዋሪ የሆነ አንድ ሰው፣ “የእነርሱስ አባት ማን ነው?” ብሎ መለሰ። ስለዚህ፣ “ሳኦልም ከነቢያት ወገን ነውን?” የሚል ምሳሌያዊ አነጋገር ሆነ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 በዚያ ነዋሪ የሆነ አንድ ሰው፥ “አባታቸውስ ማን ነው?” ብሎ መለሰ። ስለዚህ፥ “ሳኦልም ከነቢያት ወገን ነውን?” የሚል ምሳሌያዊ አነጋገር ሆነ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 በዚያም የሚኖር አንድ ሰው “የእነዚህስ የሌሎቹ ነቢያት ሁኔታ እንዴት ነው? አባቶቻቸውስ እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀ፤ “ሳኦልም ደግሞ ከነቢያት ወገን ነውን?” የሚል የምሳሌ አነጋገር የመነጨውም ከዚህ ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ከዚያም ስፍራ ያለ አንድ ሰው፦ አባታቸውስ ማን ነው? ብሎ መለሰ። ስለዚህም፦ ሳኦል ደግሞ ከነቢያት ወገን ነውን? የሚል ምሳሌ ሆነ። See the chapter |