Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ሳሙኤል 1:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በየ​ዓ​መ​ቱም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሚ​ወ​ጣ​በት ጊዜ እን​ዲህ ያደ​ርግ ነበር፤ እር​ስ​ዋም ትበ​ሳ​ጭና ታለ​ቅስ ነበር። እህ​ልም አት​በ​ላም ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ይህም በየዓመቱ ይደጋገም ነበር፤ ሐና ወደ እግዚአብሔር ቤት በምትወጣበት ጊዜ ሁሉ፣ እስክታለቅስና መብላት እስኪያቅታት ድረስ ጣውንቷ ታበሳጫት ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ወደ ጌታ ቤት በምትወጣበት ጊዜ ሁሉ ይህ በየዓመቱ ይደጋገም ነበር፤ እስክታለቅስና መብላት እስኪያቅታት ድረስ ታበሳጫት ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ይህም ሳይቋረጥ በየዓመቱ የሚደጋገም ነገር ነበር፤ ይኸውም ወደ እግዚአብሔር ቤት በሄዱ ቊጥር ሐና እያለቀሰች ምግብ ለመብላት እምቢ እስከምትል ድረስ ጵኒና በብርቱ ታበሳጫት ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በየዓመቱም እንዲህ ባደረገ ጊዜ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር በምትወጣበት ጊዜ ታበሳጫት ነበር፥ ሐናም ታለቅስ ነበር፥ አንዳችም አትቀምስም ነበር።

See the chapter Copy




1 ሳሙኤል 1:7
7 Cross References  

እና​ቱም ታናሽ መደ​ረ​ቢያ ሠራ​ች​ለት፤ በየዓ​መ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት ለመ​ሠ​ዋት ከባ​ልዋ ጋር ስት​ወጣ ትወ​ስ​ድ​ለት ነበር።


እንደ መከ​ራ​ዋና እንደ ኀዘ​ን​ዋም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ አል​ሰ​ጣ​ትም ነበር። ስለ​ዚ​ህም ታዝን ነበር። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​ፀ​ን​ዋን ዘግ​ት​ዋ​ልና፥ ልጆ​ች​ንም አል​ሰ​ጣ​ት​ምና።


ባልዋ ሕል​ቃ​ናም፥ “ሐና ሆይ!” አላት እር​ስ​ዋም፥ “ጌታዬ እነ​ሆኝ” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “ለምን ታለ​ቅ​ሻ​ለሽ? ለም​ንስ አት​በ​ዪም? ለም​ንስ ልብሽ ያዝ​ን​ብ​ሻል? እኔስ ከዐ​ሥር ልጆች አል​ሻ​ል​ሽ​ምን?” አላት።


ሕይ​ወ​ት​ህን ከጥ​ፋት የሚ​ያ​ድ​ናት፥ በይ​ቅ​ር​ታ​ውና በም​ሕ​ረቱ የሚ​ከ​ል​ልህ፥


ጢማ​ቸ​ውን ላጭ​ተው፥ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ቀድ​ደው እያ​ለ​ቀሱ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያቀ​ርቡ ዘንድ የእ​ህል ቍር​ባ​ንና ዕጣን በእ​ጃ​ቸው የያዙ፥ ሰማ​ንያ ሰዎች ከሴ​ኬ​ምና ከሴሎ፥ ከሰ​ማ​ር​ያም መጡ።


ሐናም ጸለ​የች፤ እን​ዲ​ህም አለች፦ “ልቤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸና፤ ቀን​ዴም በአ​ም​ላኬ በመ​ድ​ኀ​ኒቴ ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ ተከ​ፈተ፤ በማ​ዳ​ን​ህም ደስ ብሎ​ኛል።


ምኞ​ት​ህን ከበ​ረ​ከቱ የሚ​ያ​ጠ​ግ​ባት፥ ጐል​ማ​ስ​ነ​ት​ህን እንደ ንስር የሚ​ያ​ድ​ሳት፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements