Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ጴጥሮስ 1:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፤ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር ሳይሆን፣ ሕያው በሆነና ጸንቶ በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል አማካይነት ከማይጠፋ ዘር ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ዳግመኛ የተወለዳችሁት በሕያውና ጸንቶ በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል አማካይነት ከማይጠፋ ዘር እንጂ፤ ከሚጠፋ ዘር አይደለም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ዳግመኛ የተወለዳችሁት ሕያው በሆነውና ለዘለዓለም ጸንቶ በሚኖረው በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ ከሚጠፋ ዘር አይደለም፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።

See the chapter Copy




1 ጴጥሮስ 1:23
18 Cross References  

ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኀይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሕያው ነውና፤ የሚ​ሠ​ራም ሁለት ልሳን ካለው ሰይ​ፍም ሁሉ ይልቅ የተ​ሳለ ነው፤ ነፍ​ስ​ንና መን​ፈ​ስ​ንም፥ ጅማ​ት​ንና ቅል​ጥ​ም​ንም እስ​ኪ​ለይ ድረስ ይወ​ጋል፤ የል​ብ​ንም ስሜ​ትና አሳብ ይመ​ረ​ም​ራል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “እው​ነት እው​ነት እል​ሀ​ለሁ፤ ዳግ​መኛ ያል​ተ​ወ​ለደ ሰው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ለማ​የት አይ​ች​ልም” አለው።


እነ​ር​ሱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተወ​ለዱ እንጂ ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ግብር ወይም ከወ​ን​ድና ከሴት ፈቃድ አል​ተ​ወ​ለ​ዱም።


ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ መን​ፈስ ነው፤ ሥጋ ግን አን​ዳች አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ ይህም እኔ የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ቃል መን​ፈስ ነው፤ ሕይ​ወ​ትም ነው።


ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን።


ለፍጥረቱ የበኵራት ዐይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እው​ነት እው​ነት እል​ሀ​ለሁ፤ ዳግ​መኛ ከው​ኃና ከመ​ን​ፈስ ቅዱስ ያል​ተ​ወ​ለደ ሰው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ሊገባ አይ​ች​ልም።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም።


የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል።” በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው።


ሁሉም በእ​ርሱ ሆነ፤ ከሆ​ነ​ውም ሁሉ ያለ እርሱ ምንም የሆነ የለም።


የሚ​ያ​ልም ነቢይ ሕል​ምን ይና​ገር፤ ቃሌም ያለ​በት ቃሌን በእ​ው​ነት ይና​ገር። ገለባ ከስ​ንዴ ጋር ምን አለው? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የማ​ይ​ሞ​ተ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር በሚ​ሞት ሰውና በዎ​ፎች፥ አራት እግር ባላ​ቸ​ውም፥ በሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ትም መልክ መስ​ለው ለወጡ።


እነሆ፥ ክንዳችሁን እገሥጻለሁ፥ የመሥዋዕታችሁንም ፋንድያ በፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፣ ከእርሱም ጋር በአንድነት ትወሰዳላችሁ።


ምሳ​ሌ​ዉም ይህ ነው፤ ዘሩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ነው፤


ከበ​ድ​ና​ቸ​ውም በሚ​ዘራ ዘር ላይ አን​ዳች ቢው​ድቅ እርሱ ንጹሕ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements