Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ነገሥት 5:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ኪራ​ምም እን​ዲህ ሲል ወደ ሰሎ​ሞን ላከ፥ “የላ​ክ​ህ​ብ​ኝን ሁሉ ሰማሁ፤ ስለ ዝግ​ባ​ውና ስለ ጥዱ እን​ጨት ፈቃ​ድ​ህን ሁሉ አደ​ር​ጋ​ለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስለዚህ ኪራም፣ ለሰሎሞን እንዲህ ሲል ላከበት፤ “የላክኸው መልእክት ደርሶኛል፤ የዝግባውንና የጥዱን ግንድ በማቅረብ ረገድ የምትፈልገውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከዚህ በኋላ ኪራም ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ለሰሎሞን ላከ፦ “ያስተላለፍከው መልእክት ደርሶኛል፤ አንተ የምትፈልገውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ፤ የሊባኖሱን ዛፍና የዝግባውን ግንድ አዘጋጅቼ አቀርብልሃለሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከዚህ በኋላ ኪራም ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ለሰሎሞን ላከ “ያስተላለፍከው መልእክት ደርሶኛል፤ አንተ የምትፈልገውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ፤ የሊባኖሱን ዛፍና የዝግባውን ግንድ አዘጋጅቼ አቀርብልሃለሁ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ኪራምም “የላክህብኝን ሁሉ ሰማሁ፤ ስለ ዝግባውና ስለ ጥዱ እንጨት ፈቃድህን ሁሉ አደርጋለሁ።

See the chapter Copy




1 ነገሥት 5:8
7 Cross References  

ታላ​ቁ​ንም ቤት በዝ​ግባ እን​ጨት ከደ​ነው፤ በጥ​ሩም ወርቅ ለበ​ጠው፤ የዘ​ን​ባ​ባና የሰ​ን​ሰ​ለት አም​ሳ​ልም ቀረ​ጸ​በት።


ሁለ​ቱ​ንም ደጆች ከጥድ እን​ጨት ሠራ፤ አንዱ ደጅ በማ​ጠ​ፊያ ከተ​ያ​ያዙ ከሁ​ለት ሣን​ቃ​ዎች ተሠራ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ደጅ በማ​ጠ​ፊያ ከተ​ያ​ያዙ ከሁ​ለት ሣን​ቃ​ዎች ተሠራ።


የቤ​ቱ​ንም ግንብ ውስ​ጡን በዝ​ግባ ሳንቃ ለበጠ፤ ከቤ​ቱም መሠ​ረት ጀምሮ እስከ ጣራው ድረስ የው​ስ​ጡን ግንብ በእ​ን​ጨት ለበ​ጠው፤ ደግ​ሞም የቤ​ቱን ወለል በጥድ እን​ጨት አነ​ጠ​ፈው።


ዳዊ​ትና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣ​ሪ​ያ​ዎች በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ፥ በከ​በ​ሮና በነ​ጋ​ሪት፥ በጸ​ና​ጽ​ልና በዕ​ን​ዚራ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሙሉ ኀይ​ላ​ቸው ይጫ​ወቱ ነበር።


ኪራ​ምም የሰ​ሎ​ሞ​ንን ቃል ሰምቶ እጅግ ደስ አለ​ውና፥ “በዚህ ታላቅ ሕዝብ ላይ ጥበ​በኛ ልጅ ለዳ​ዊት የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ይመ​ስ​ገን” አለ።


አገ​ል​ጋ​ዮቼ ከሊ​ባ​ኖስ ወደ ባሕር ያወ​ር​ዱ​ል​ሃል፤ እኔም በመ​ር​ከብ አድ​ርጌ በባ​ሕር ላይ እያ​ን​ሳ​ፈ​ፍሁ አንተ እስከ ወሰ​ን​ኸው ስፍራ ድረስ አደ​ር​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ በዚ​ያም እፈ​ታ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተም ከዚያ ታስ​ወ​ስ​ደ​ዋ​ለህ፤ አን​ተም ፈቃ​ዴን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ለቤተ ሰቦ​ቼም ቀለብ የሚ​ሆ​ነ​ውን ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ።”


እኛም ከሊ​ባ​ኖስ የም​ት​ሻ​ውን ያህል እን​ጨት እን​ቈ​ር​ጣ​ለን፤ በታ​ን​ኳም አድ​ር​ገን በባ​ሕር ላይ ወደ አንተ ወደ ኢዮጴ እን​ል​ካ​ለን፤ አን​ተም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ታስ​ወ​ስ​ደ​ዋ​ለህ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements