Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ነገሥት 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ግሩ በታች እስ​ኪ​ጥ​ል​ለት ድረስ በዙ​ሪ​ያው ስለ ነበረ ጦር​ነት አባቴ ዳዊት ለአ​ም​ላኩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት መሥ​ራት እን​ዳ​ል​ቻለ አንተ ታው​ቃ​ለህ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 “አባቴ ዳዊት በዙሪያው ሁሉ ከገጠመው ጦርነት የተነሣ፣ እግዚአብሔር ጠላቶቹን ከእግሩ በታች እስኪጥልለት ድረስ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስ መሥራት እንዳልቻለ ታውቃለህ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 “አባቴ ዳዊት በዙሪያው ከነበሩት የጠላት አገሮች ሠራዊት ጋር ሲዋጋ መኖሩን አንተ ራስህ ታውቀዋለህ፤ በጠላቶቹ ላይ ጌታ ድልን እስኪያጐናጽፈው ድረስ ለእግዚአብሔር ለጌታው ቤተ መቅደስ ለመሥራት አለመቻሉንም ታስታውሳለህ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “አባቴ ዳዊት በዙሪያው ከነበሩት የጠላት አገሮች ሠራዊት ጋር ሲዋጋ መኖሩን አንተ ራስህ ታውቀዋለህ፤ በጠላቶቹ ላይ ድልን እስኪያጐናጽፈው ድረስ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ለመሥራት አለመቻሉንም ታስታውሳለህ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 “እግዚአብሔር ከእግሩ በታች እስኪጥልለት ድረስ በዙሪያው ስለ ነበረ ሰልፍ አባቴ ዳዊት የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት እንዳልቻለ አንተ ታውቃለህ።

See the chapter Copy




1 ነገሥት 5:3
17 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን፦ የሰ​ልፍ ሰው ነህና፥ ብዙ ደምም አፍ​ስ​ሰ​ሃ​ልና ስሜ የሚ​ጠ​ራ​በ​ትን ቤት አት​ሠ​ራም ብሎ​ኛል።


ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እን​ዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ እጅግ ብዙ ደም አፍ​ስ​ሰ​ሃል፤ ታላ​ቅም ሰልፍ አድ​ር​ገ​ሃል፤ በፊ​ቴም በም​ድር ላይ ብዙ ደም አፍ​ስ​ሰ​ሃ​ልና ለስሜ ቤት አት​ሠ​ራም።


ጠላ​ቶቹ ሁሉ ከእ​ግሩ በታች እስ​ኪ​ወ​ድቁ ድረስ ይነ​ግሥ ዘንድ አለ​ውና።


በምሠራበት ቀን በደለኞች ከእግራችሁ ጫማ በታች አመድ ይሆናሉና እናንተ ትረግጡአቸዋላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


አቤቱ፥ በቅ​ኖች ሸንጎ በጉ​ባ​ኤም በፍ​ጹም ልቤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


በእ​ጆ​ች​ህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾም​ኸው፤ ሁሉን ከእ​ግ​ሮቹ በታች አስ​ገ​ዛ​ህ​ለት፥


እነ​ዚ​ያ​ንም ነገ​ሥት ወደ ኢያሱ ባመ​ጡ​አ​ቸው ጊዜ ኢያሱ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች ሁሉ ጠራ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የሄ​ዱ​ትን የተ​ዋ​ጊ​ዎ​ችን አለ​ቆች “ቅረቡ፤ በእ​ነ​ዚ​ህም ነገ​ሥት አን​ገት ላይ እግ​ራ​ች​ሁን አኑሩ” አላ​ቸው። ቀረ​ቡም በአ​ን​ገ​ታ​ቸ​ውም ላይ እግ​ራ​ቸ​ውን አኖሩ።


ሁሉ​ንም ከእ​ግሩ በታች አድ​ርጎ አስ​ገ​ዛ​ለት፤ ከሁሉ በላይ የሆነ እር​ሱን ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ራስ አደ​ረ​ገው።


ነገር ግን ከወ​ገ​ብህ የሚ​ወ​ጣው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል እንጂ ቤት የም​ት​ሠ​ራ​ልኝ አንተ አይ​ደ​ለ​ህም” አለው።


ንጉ​ሡም ዳዊት በጉ​ባ​ኤው መካ​ከል ቆሞ እን​ዲህ አለ፥ “ወን​ድ​ሞቼና ሕዝቤ ሆይ፥ ስሙኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦ​ትና ለአ​ም​ላ​ካ​ችን እግር ማረ​ፊያ የዕ​ረ​ፍት ቤት ለመ​ሥ​ራት አሳብ በልቤ መጣ​ብኝ፤ ለዚ​ህም ሥራ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውን አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤


ዋልያ፥ ሚዳቋ፥ የበ​ረሃ ፍየል፥ ጎሽ፥ ብሖር፥ ሳላ፥ ድኵላ።


የማ​ዕ​ዱ​ንም መብል፥ የብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹ​ንም አቀ​ማ​መጥ፥ የሎ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም ሥር​ዐት፥ አለ​ባ​በ​ሳ​ቸ​ው​ንም፥ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ቹ​ንም፥ አለ​ባ​በ​ሳ​ቸ​ው​ንም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የሚ​ያ​ሳ​ር​ገ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ባየች ጊዜ ተደ​ነ​ቀች።


ደግ​ሞም በዙ​ሪ​ያ​ችን ካሉት አሕ​ዛብ ወደ እኛ ከመ​ጡት ሌላ ከአ​ይ​ሁ​ድና ከሹ​ሞቹ መቶ አምሳ ሰዎች በገ​በ​ታዬ ነበሩ።


ለአ​ንድ ቀን አንድ በሬና ስድ​ስት የሰቡ በጎች፥ አንድ ፍየ​ልም፥ በዐ​ሥር በዐ​ሥር ቀንም ብዙ ልዩ ልዩ ዓይ​ነት ወይን ጠጅ ይዘ​ጋ​ጅ​ልኝ ነበር፤ ነገር ግን አገ​ዛዝ በሕ​ዝቡ ላይ ከብዶ ነበ​ርና ለአ​ለቃ የሚ​ገ​ባ​ውን ቀለብ አል​ሻም ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements