Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ነገሥት 13:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከዚ​ህም በኋላ ንጉሡ ኢዮ​ር​ብ​ዓም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በቤ​ቴል ባለው መሠ​ዊያ ላይ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር በሰማ ጊዜ፥ ንጉሡ፥ “ያዙት” ብሎ እጁን ከመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ አነሣ። ከዚ​ህም በኋላ በእ​ርሱ ላይ የዘ​ረ​ጋት እጁ ደረ​ቀች፤ ወደ እር​ሱም ይመ​ል​ሳት ዘንድ አል​ተ​ቻ​ለ​ውም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ንጉሥ ኢዮርብዓምም ያ የእግዚአብሔር ሰው በቤቴል መሠዊያ ላይ ጮኾ የተናገረውን ሲሰማ፣ እጁን መሠዊያው ካለበት በመዘርጋት፣ “ያዙት!” አለ፤ ነገር ግን ያች የዘረጋት እጁ ደርቃ ቀረች፤ ሊመልሳትም አልቻለም

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ እጁን አንሥቶ ወደ ነቢዩ በማመልከት! “ያዙት!” የሚል ትእዛዝ ሰጠ፤ የንጉሡም ክንድ ወዲያውኑ ድርቅ ብሎ ሽባ ስለ ሆነ የዘረጋውን እጁን መመለስ አልቻለም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ንጉሥ ኢዮርብዓምም ይህን በሰማ ጊዜ እጁን አንሥቶ ወደ ነቢዩ በማመልከት! “ያዙት!” የሚል ትእዛዝ ሰጠ፤ የንጉሡም ክንድ ወዲያውኑ ድርቅ ብሎ ሽባ ስለ ሆነ የዘረጋውን እጁን መመለስ አልቻለም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ንጉሡም የእግዚአብሔር ሰው በቤቴል ባለው መሠዊያ ላይ የጮኸውን ነገር በሰማ ጊዜ፥ ኢዮርብዓም እጁን ከመሠዊያው አንሥቶ “ያዙት!” አለ። በእርሱም ላይ የዘረጋት እጅ ደረቀች፤ ወደ እርሱም ይመልሳት ዘንድ አልተቻለውም።

See the chapter Copy




1 ነገሥት 13:4
26 Cross References  

ማንምም ሊጐዳቸው ቢወድ እሳት ከአፋቸው ይወጣል፤ ጠላቶቻቸውንም ይበላል፤ ማንም ሊጐዳቸው ቢወድም እንዲሁ ሊገደል ይገባዋል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ ነኝ” ባላ​ቸው ጊዜ፤ ወደ ኋላ​ቸው ተመ​ል​ሰው በም​ድር ላይ ወደቁ።


እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ የም​ል​ከ​ውን የሚ​ቀ​በል እኔን ይቀ​በ​ላል፤ እኔ​ንም የሚ​ቀ​በል የላ​ከ​ኝን ይቀ​በ​ላል።”


እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ ወደ እነ​ር​ሱም ዙሮ ከተ​መ​ለ​ከተ በኋላ፦ ያን ሰው፥ “እጅ​ህን ዘርጋ” አለው፤ ሰው​ዬ​ውም ዘረ​ጋት፤ እጁም ዳነ​ችና እንደ ሁለ​ተ​ኛ​ይቱ ሆነች።


ኢየሱስን የያዙትም ጻፎችና ሽማግሎች ወደ ተከማቹበት ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ወሰዱት።


ንጉሡም መልሶ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት፤’ ይላቸዋል።


የለ​መ​ኑ​ት​ንም ሰጣ​ቸው፤ ለነ​ፍ​ሳ​ች​ውም ጥጋ​ብን ላከ።


አሳም በነ​ቢዩ በአ​ናኒ ላይ ተቈጣ፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር ተቈ​ጥ​ቶ​አ​ልና በግ​ዞት አኖ​ረው፤ በዚ​ያን ጊዜም አሳ ከሕ​ዝቡ አያሌ ሰዎ​ችን አስ​ጨ​ነቀ።


በቤቱ ደጃፍ የነ​በ​ሩ​ት​ንም ሰዎች ከታ​ና​ሻ​ቸው ጀምሮ እስክ ታላ​ቃ​ቸው ድረስ ዐይ​ና​ቸ​ውን አሳ​ወ​ሩ​አ​ቸው፤ ደጃ​ፉ​ንም ሲፈ​ልጉ ደከሙ፤ አጡ​ትም።


በዚ​ያም ቀን፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው፤ “እነሆ፥ መሠ​ዊ​ያው ይሰ​ነ​ጠ​ቃል፤ በው​ስ​ጡም ያለው ስብ ይፈ​ስ​ሳል” ብሎ ምል​ክት ሰጠ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ሰጠው ምል​ክት መሠ​ዊ​ያው ተሰ​ነ​ጠቀ፤ በው​ስ​ጡም ያለው ስብ ፈሰሰ።


አን​ዱን በቤ​ቴል ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም በዳን አኖረ።


ንጉሡ እን​ዲህ ይላል፦ በደ​ኅና እስ​ክ​መ​ለስ ድረስ ይህን ሰው በግ​ዞት አኑ​ሩት፤ የመ​ከ​ራም እን​ጀራ መግ​ቡት፤ የመ​ከ​ራም ውኃ አጠ​ጡት በሉ​አ​ቸው” አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements