Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ነገሥት 1:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 ሰሎ​ሞ​ንም፥ “እርሱ አካ​ሄ​ዱን ያሳ​መረ እንደ ሆነ ከእ​ርሱ አን​ዲት ጠጕር እንኳ በም​ድር ላይ አት​ወ​ድ​ቅም፤ ነገር ግን ክፋት የተ​ገ​ኘ​በት እንደ ሆነ ይሞ​ታል” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 ሰሎሞንም፣ “አካሄዱን ካሳመረ ከራስ ጠጕሩ አንዲቱ እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም፤ ጥፋት ከተገኘበት ግን ይሞታል” ሲል መለሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 ሰሎሞንም፦ “እርሱ አካሄዱን ያሳመረ እንደሆነ ከእርሱ አንዲት ጠጉር እንኳ በምድር ላይ አትወድቅም፥ ነገር ግን ክፋት የተገኘበት እንደሆነ ይሞታል” አለ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 ንጉሥ ሰሎሞንም “አካሄዱን ካሳመረ ከራስ ጠጒሩ አንዲት እንኳ አትነካበትም፤ ክፉ ሆኖ ከተገኘ ግን ይሞታል” ሲል መለሰ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

52 ሰሎሞንም “እርሱ አካሄዱን ያሳመረ እንደ ሆነ ከእርሱ አንዲት ጠጕር እንኳ በምድር ላይ አትወድቅም፤ ነገር ግን ክፋት የተገኘበት እንደ ሆነ ይሞታል፤” አለ።

See the chapter Copy




1 ነገሥት 1:52
11 Cross References  

ሕዝ​ቡም ሳኦ​ልን፥ “በውኑ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ታላቅ መድ​ኀ​ኒት ያደ​ረገ ዮና​ታን ዛሬ ይሞ​ታ​ልን? ይህ አይ​ሁን፤ ዛሬ ለሕ​ዝቡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አድ​ር​ጎ​አ​ልና ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ከራሱ ጠጕር አን​ዲት በም​ድር ላይ አት​ወ​ድ​ቅም” አሉት። ሕዝ​ቡም ያን ጊዜ ስለ ዮና​ታን ጸለዩ፤ እር​ሱም አል​ተ​ገ​ደ​ለም።


ያችም ሴት፥ “ለመ​ግ​ደል ባለ ደሞች እን​ዳ​ይ​በዙ፤ ልጄ​ንም እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉ​ብኝ ንጉሥ ፈጣ​ሪው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያስብ” አለች። እር​ሱም፥ “የል​ጅ​ሽስ አን​ዲት የራሱ ጠጕር በም​ድር ላይ እን​ዳ​ት​ወ​ድቅ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን” አላት።


መንገዳቸው ቀና የሆነውን የዋሃንን ጽድቅ ትጠብቃቸዋለች፤ ኀጢአተኞችን ግን ኀጢአታቸው በደለኛ ታደርጋቸዋለች።


የክፉዎች ልብ ጽድቅን አያውቅም፥ ክፋትም ኃጥአንን ያከፋቸዋል።


ከጨ​ለማ ተመ​ልሶ እን​ዲ​ወጣ ተስፋ የለ​ውም፥ ለሰ​ይ​ፍም ኀይል ፈጽሞ ተዳ​ር​ጎ​አል።


አሁ​ንም እሺ በሉ​ኝና ምግብ ብሉ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም አድኑ፥ ከእ​ና​ንተ ከአ​ንዱ የራስ ጠጕር እንኳ አት​ጠ​ፋ​ምና።”


ነገር ግን ከራስ ጠጕ​ራ​ችሁ አን​ዲቱ እንኳ አት​ጠ​ፋም።


የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቍኦጥሮአል።


ለሰ​ሎ​ሞ​ንም፥ “እነሆ፥ አዶ​ን​ያስ ንጉ​ሡን ሰሎ​ሞ​ንን ፈርቶ፦ ንጉሡ ሰሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዩን በሰ​ይፍ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለኝ ዛሬ ይማ​ል​ልኝ ብሎ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀንድ ይዞ​አል” አሉት።


ንጉሡ ሰሎ​ሞ​ንም ላከ፤ ከመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም አወ​ረ​ዱት፤ መጥ​ቶም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ሰገደ፤ ሰሎ​ሞ​ንም፥ “ወደ ቤትህ ሂድ” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements