Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ዮሐንስ 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ስለ ልጁ የመሰከረው የእግዚአብሔር ምስክር ይህ ነውና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የሰውን ምስክርነት ከተቀበልን፣ የእግዚአብሔር ምስክርነት ከዚያም ይልቃል፤ ይህ ስለ ልጁ የሰጠው የእግዚአብሔር ምስክርነት ነውና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የሰውን ምስክርነት የምንቀበል ከሆነ የእግዚአብሔር ምስክርነት ይበልጣል፤ እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረው ምስክርነት ይህ ነውና።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሰዎች የሚሰጡትን ምስክርነት እንቀበላለን፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ምስክርነት ከሁሉ ይበልጣል። እግዚአብሔር ስለ ልጁ የሰጠውም ምስክርነት ይህ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ስለ ልጁ የመሰከረው የእግዚአብሔር ምስክር ይህ ነውና።

See the chapter Copy




1 ዮሐንስ 5:9
13 Cross References  

በመ​ረ​ጠው ሰው እጅ በዓ​ለም በእ​ው​ነት የሚ​ፈ​ር​ድ​ባ​ትን ቀን ወስ​ኖ​አ​ልና፤ እር​ሱን ከሙ​ታን ለይቶ በማ​ስ​ነ​ሣ​ቱም ብዙ​ዎ​ችን ወደ ሃይ​ማ​ኖት መል​ሶ​አ​ልና።”


እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።


በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ራሱ ፈቃድ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ጸጋ በመ​ስ​ጠት፥ በም​ል​ክ​ትና በድ​ንቅ ነገር፥ በልዩ ልዩ ተአ​ም​ራ​ትም መሰ​ከ​ረ​ላ​ቸው፤ ነገ​ራ​ቸ​ው​ንም አስ​ረ​ዳ​ላ​ቸው።


እኛም ለዚህ ነገር ምስ​ክ​ሮቹ ነን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ታ​ዘ​ዙት የሰ​ጣ​ቸው መን​ፈስ ቅዱ​ስም ምስ​ክር ነው።”


ከሠ​ራሁ ግን፥ እኔን እን​ኳን ባታ​ምኑ እኔ በአብ እን​ዳ​ለሁ አብም በእኔ እን​ዳለ ታው​ቁና ትረዱ ዘንድ ሥራ​ዬን እመኑ።”


መጻ​ሕ​ፍ​ትን መር​ምሩ፤ በእ​ነ​ርሱ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን የም​ታ​ገኙ ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልና፤ እነ​ር​ሱም የእኔ ምስ​ክ​ሮች ናቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይ​ቻ​ልም፤ በእ​ርሱ ለተ​ማ​ፀን ተጠ​ብ​ቆ​ልን ባለ ተስ​ፋ​ች​ንም ማመ​ንን ላጸ​ናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።


የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements