Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ቆሮንቶስ 7:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሌላ​ውን ግን ከራሴ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ከጌ​ታ​ች​ንም አይ​ደ​ለም፤ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን መካ​ከል የማ​ታ​ምን፥ ባል​ዋ​ንም የም​ታ​ፈ​ቅር ከእ​ር​ሱም ጋር ለመ​ኖር የም​ት​ወድ ሚስት ያለ​ችው ሰው ቢኖር ሚስ​ቱን አይ​ፍታ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ለሌሎች ደግሞ እንዲህ እላለሁ፤ ይህንም የምለው እኔ እንጂ ጌታ አይደለም። ያላመነች ሚስት ያለው ወንድም ቢኖርና ሚስቱ ዐብራው ለመኖር የምትፈቅድ ከሆነ፣ ሊፈታት አይገባውም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሌሎችንም፥ ጌታም አይደለም፥ እኔ እላለሁ፤ ከወንድሞች ወገን ያላመነች ሚስት ያለችው ቢኖር፥ እርሷም ከእርሱ ጋር ለመኖር ብትስማማ፥ አይፍታት፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ለሌሎቹ ግን ጌታ ሳይሆን እኔ ራሴ የምለው እንዲህ ነው፤ አንድ ክርስቲያን ሰው ክርስቲያን ያልሆነች ሚስት ብትኖረውና አብራው ለመኖር ብትፈልግ አይፍታት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሌሎችንም እኔ እላለሁ፥ ጌታም አይደለም፤ ከወንድሞች ወገን ያላመነች ሚስት ያለችው ቢኖር እርስዋም ከእርሱ ጋር ልትቀመጥ ብትስማማ፥ አይተዋት፤

See the chapter Copy




1 ቆሮንቶስ 7:12
8 Cross References  

ይህም ቢሆን የም​ና​ገ​ረው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገባ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ስለ​ዚ​ህች ትም​ክ​ሕቴ እንደ ሰነፍ እና​ገ​ራ​ለሁ።


ይህ​ንም የም​ላ​ችሁ እንደ ፈቃድ ነው እንጂ፥ ላዝ​ዛ​ችሁ አይ​ደ​ለም።


ስለ ደና​ግ​ልም የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ አይ​ደ​ለም፤ ታማኝ እን​ድ​ሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ያለኝ እንደ መሆኔ ምክ​ሬን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ።


ከተ​ፋ​ታ​ችም ብቻ​ዋን ትኑር፤ ያለ​ዚያ ከባ​ልዋ ጋር ትታ​ረቅ፤ ባልም ሚስ​ቱን አይ​ፍታ።


ሴቲ​ቱም የማ​ያ​ም​ንና ሚስ​ቱ​ንም የሚ​ያ​ፈ​ቅር ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ሊኖር የሚ​ወድ ባል ቢኖ​ራት ባል​ዋን አት​ፍታ።


ከሚ​ስ​ትህ ጋር ሳለህ ከእ​ር​ስዋ መፋ​ታ​ትን አትሻ፤ ሚስት ከሌ​ለህ ግን ሚስ​ትን አትሻ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements