Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ቆሮንቶስ 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እኔ በሥ​ጋዬ ከእ​ና​ንተ ጋር ባል​ኖር፥ በመ​ን​ፈሴ ከእ​ና​ንተ ጋር አለሁ፤ እነሆ፥ ከእ​ና​ንተ ጋር እንደ አለሁ ሆኜ፥ ይህን ሥራ የሠ​ራ​ውን እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ምንም እንኳ እኔ በአካል አብሬያችሁ ባልሆንም፣ በመንፈስ ግን ከእናንተ ጋራ ነኝ፤ ልክ አብሬያችሁ እንዳለሁ ሆኜ፣ ይህን ባደረገው ሰው ላይ አሁኑኑ ፈርጄበታለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እኔ ምንም እንኳ በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ከእናንተ ጋር እንደ አለሁ ሆኜ፥ ይህን ሥራ የሠራውን እፈርድበታለሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ምንም እንኳ እኔ በሥጋ አብሬአችሁ ባልሆን በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ልክ አብሬአችሁ እንዳለሁ ሆኜ እንዲህ ዐይነቱን ሥራ በፈጸመው ሰው ላይ በጌታ በኢየሱስ ስም ፈርጄበታለሁ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3-4 እኔ ምንም እንኳ በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፥ ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን እንደዚህ በሠራው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ፤ እናንተና መንፈሴም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር ተሰብስበን፥

See the chapter Copy




1 ቆሮንቶስ 5:3
6 Cross References  

እኔ በሥጋ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ባል​ኖ​ርም እን​ኳን፥ በመ​ን​ፈስ ከእ​ና​ንተ ጋር ነኝ፤ እነሆ ጠባ​ያ​ች​ሁ​ንና ሥር​ዐ​ታ​ች​ሁን፥ በክ​ር​ስ​ቶ​ስም ያለ የእ​ም​ነ​ታ​ች​ሁን ጽናት ስለ አየሁ ደስ ይለ​ኛል።


እኛ ግን ወንድሞች ሆይ! በልብ ያይደለ ፊት ለፊት ለጥቂት ጊዜ አጥተናችሁ፥ በብዙ ናፍቆት ፊታችሁን ለማየት እጅግ ሞከርን፤


ጥን​ቱን አስ​ቀ​ድሜ ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አሁ​ንም አስ​ቀ​ድሜ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ቀድሞ ከእ​ና​ንተ ጋር ሳለሁ እንደ ነገ​ር​ሁ​አ​ችሁ፥ አስ​ቀ​ድሞ ለበ​ደሉ፥ ለሌ​ሎ​ችም ሁሉ እንደ ገና የመ​ጣሁ እንደ ሆነ ርኅ​ራኄ እን​ዳ​ላ​ደ​ርግ፥ እን​ዲሁ ሳል​ኖር ለሦ​ስ​ተኛ ጊዜ እና​ገ​ራ​ለሁ፥


ነገር ግን ይህን ነገር የሚ​ና​ገር ይህን ይወቅ፤ በሌ​ለ​ን​በት ጊዜ በመ​ል​እ​ክ​ታ​ችን እንደ ተገ​ለ​ጠው እንደ ቃላ​ችን፥ ባለ​ን​በ​ትም ጊዜ በሥ​ራ​ችን እን​ዲሁ ነን።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ ጳው​ሎስ በእ​ና​ንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆ​ንሁ፥ ከእ​ና​ንተ ብርቅ ግን የም​ደ​ፍ​ራ​ችሁ በክ​ር​ስ​ቶስ የዋ​ህ​ነ​ትና ቸር​ነት እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፥ በፍ​ቅ​ራ​ችሁ እታ​መ​ና​ለ​ሁና።


ምን አግ​ዶኝ፥ በውጭ ባለው ላይ እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ? እና​ን​ተስ በው​ስጥ ከእ​ና​ንተ ጋር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ፈር​ዳ​ችሁ ቅጡ​አ​ቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements