1 ቆሮንቶስ 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 እናንተም ከዚህ ጋር ትዕቢተኞች ናችሁ፤ ይልቁንም ይህን ያደረገው ከእናንተ ይለይ ዘንድ ለምን አላዘናችሁበትም? See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ደግሞም ታብያችኋል! ይልቅስ ሐዘን ተሰምቷችሁ፣ ይህን ድርጊት የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ ልታስወግዱት አይገባምን? See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 እናንተም ታብያችኋል፤ ይልቅስ ልታዝኑ አይገባችሁም? ይህን ሥራ የሠራው ከመካከላችሁ ይወገድ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ታዲያ፥ እንዲህ ያለ አሳፋሪ ነገር በመካከላችሁ እያለ ለምን ትታበያላችሁ? ይልቅስ በዚህ ነገር ማዘን አይገባችሁምን? እንዲህ ዐይነቱን ሥራ የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ አስወግዱ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እናንተም ታብያችኋል፤ ይልቅስ እንድታዝኑ አይገባችሁምን? ይህን ሥራ የሠራው ከመካከላችሁ ይወገድ። See the chapter |