Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




1 ቆሮንቶስ 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እኔስ ለሞት ዝግ​ጁ​ዎች እንደ መሆ​ና​ችን እኛን ሐዋ​ር​ያ​ቱን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኋ​ለ​ኞች ያደ​ረ​ገን ይመ​ስ​ለ​ኛል፤ እኛ ለሰ​ዎ​ችም፥ ለአ​ለ​ቆ​ችም፥ ለዓ​ለ​ምም መዘ​ባ​በቻ ሆነ​ና​ልና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ምክንያቱም እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን፣ ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሰው ሁሉ መጨረሻ ያሰለፈን ይመስለኛል፤ ለዓለም ሁሉ፣ ለመላእክትም ለሰዎችም ትርኢት ሆነናል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሁሉ ይልቅ የኋለኞች እንዳደረገን ይመስለኛል፤ ምክንያቱም ለዓለም ለመላእክትም ለሰዎችም ትንግርት ሆነናል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት ተፈርዶባቸው ወደሚገደሉበት ቦታ ከሚወሰዱት ሰዎች መካከል የመጨረሻዎቹ ያደረገን ይመስለኛል፤ ከዚህም የተነሣ በዓለም ሁሉ በመላእክትም ሆነ በሰዎች ፊት እንደ ትርኢት ሆነን እንታያለን፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ለዓለም ለመላእክትም ለሰዎችም መጫወቻ ሆነናልና፤ እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሁሉ ይልቅ የኋለኞች እንዳደረገን ይመስለኛልና።

See the chapter Copy




1 ቆሮንቶስ 4:9
21 Cross References  

እና​ንተ ተሰ​ድ​ባ​ችሁ ነበር፤ መከ​ራም አጽ​ን​ተ​ው​ባ​ችሁ ነበር፤ ተዘ​ባ​ብ​ተ​ው​ባ​ች​ሁም ነበር፤ በዚ​ህም መን​ገድ እን​ዲህ ከሆ​ኑት ጋር ተባ​ብ​ራ​ችሁ ነበር።


መጽ​ሐፍ እን​ዳለ፥ “ስለ አንተ ዘወ​ትር ይገ​ድ​ሉ​ናል፤ እን​ደ​ሚ​ታ​ረዱ በጎ​ችም ሆነ​ናል።”


መላ​እ​ክት ሁሉ መና​ፍ​ስት አይ​ደ​ሉ​ምን? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይወ​ርሱ ዘንድ ስለ አላ​ቸው ሰዎ​ችስ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ይላኩ የለ​ምን?


የገ​ረ​ፉ​አ​ቸው፥ የዘ​በ​ቱ​ባ​ቸ​ውና ያሠ​ሩ​አ​ቸው ወደ ወህኒ ያገ​ቡ​አ​ቸ​ውም አሉ።


በዚህ መከራ ማንም እንዳይናወጥ፥ ለዚህ እንደ ተመረጥን ራሳችሁ ታውቃላችሁና።


እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቁ ስን​ታይ የታ​ወ​ቅን ነን፤ እንደ ሰነ​ፎች ስን​ታ​ይም ልባ​ሞች ነን፤ እንደ ሙታን ስን​ታይ ሕያ​ዋን ነን፤ የተ​ቀ​ጣን ስን​ሆ​ንም አን​ገ​ደ​ልም።


ከእ​ስ​ያም የሆኑ ታላ​ላ​ቆች ወዳ​ጆቹ ወደ ጨዋ​ታው ቦታ እን​ዳ​ይ​ገባ ልከው ማለ​ዱት።


ከተ​ማ​ውም ሁሉ ታወከ፤ የመ​ቄ​ዶ​ን​ያን ሰዎች የጳ​ው​ሎ​ስን ወዳ​ጆች ጋይ​ዮ​ስ​ንና አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮ​ስ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ጋር እየ​ጐ​ተ​ቱ​በ​አ​ን​ድ​ነት ወደ ጨዋ​ታው ቦታ ሮጡ።


በዘ​መ​ኑም ጽድቅ ይበ​ቅ​ላል፥ ጨረ​ቃም እስ​ኪ​ያ​ልፍ ድረስ ሰላም ብዙ ነው።


ድካ​ም​ንና ጣርን አይ ዘንድ፥ ዘመ​ኔም በእ​ፍ​ረት ታልቅ ዘንድ ስለ ምን ከማ​ኅ​ፀን ወጣሁ?


በዚህ ዓለም ሕይ​ወት ብቻ ክር​ስ​ቶ​ስን ተስፋ ከአ​ደ​ረ​ግ​ነው ከሰው ሁሉ ይልቅ ጉዳ​ተ​ኞች ነን።


እነ​ርሱ የክ​ር​ስ​ቶስ አገ​ል​ጋ​ዮች ቢሆ​ኑም እኔም እንደ ሰነፍ ለራሴ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ እኔ እበ​ል​ጣ​ለሁ፤ እጅ​ግም ደከ​ምሁ፤ ብዙ ጊዜ ተገ​ረ​ፍሁ፤ ብዙ ጊዜም ታሰ​ርሁ፤ ብዙ ጊዜም ለሞት ተዘ​ጋ​ጀሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements