Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 72:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ተራሮች ብልጽግናን፣ ኰረብቶችም የጽድቅን ፍሬ ለሕዝቡ ያመጣሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በጽድቅ፥ ተራሮችና ኰረብቶች ለሕዝብህ ሰላምን ይቀበሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ተራራዎች ብልጽግናን፥ ኰረብቶችም የጽድቅ ፍሬን ለሕዝብ ያስገኙ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የዐ​መ​ፀ​ኞ​ችን ሰላም አይቼ በኃ​ጥ​ኣን ላይ ቀንቼ ነበ​ርና።

See the chapter Copy




መዝሙር 72:3
13 Cross References  

በተራሮች ላይ የቆሙ፣ የምሥራችን የሚያመጡ እግሮች፣ ሰላምን የሚናገሩ፣ መልካም ዜና የሚያበሥሩ፣ ድነትን የሚያውጁ፣ ጽዮንንም፣ “አምላክሽ ነግሧል!” የሚሉ እንዴት ያማሩ ናቸው።


“በዚያ ጊዜ ተራሮች፣ አዲስ የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፤ ኰረብቶችም ወተት ያፈስሳሉ፤ በይሁዳ ያሉ ሸለቆዎች ሁሉ ውሃ ያጐርፋሉ፤ ከእግዚአብሔር ቤት ምንጭ ይፈልቃል፤ የሰጢምን ሸለቆ ያጠጣል።


“ዐመፃን ለማስቆም፣ ኀጢአትን ለማስወገድ፣ በደልን ለማስተስረይ፣ ዘላለማዊ ጽድቅን ለማምጣት፣ ራእይንና ትንቢትን ለማተምና፣ እጅግ ቅዱስ የሆነውን ለመቀባት ስለ ሕዝብህና ስለ ተቀደሰችው ከተማህ ሰባ ሱባዔ ታውጇል።


በምድሪቱ ላይ እህል ይትረፍረፍ፤ በተራሮችም ዐናት ላይ ይወዛወዝ። ፍሬው እንደ ሊባኖስ ይንዠርገግ፤ በከተማ ያለውም እንደ ሜዳ ሣር እጅብ ብሎ ይውጣ።


የምድረ በዳው ሣር እጅግ ለመለመ፤ ኰረብቶችም ደስታን ተጐናጸፉ።


“እናንተ ሰማያት፣ ጽድቅን ከላይ አዝንቡ፤ ደመናትም ወደ ታች አንጠብጥቡ፤ ምድር ትከፈት፤ ድነት ይብቀል፤ ጽድቅም ዐብሮት ይደግ፤ እኔ እግዚአብሔር ፈጥሬዋለሁ።


በናስ ፈንታ ወርቅ፣ በብረትም ፈንታ ብር አመጣልሻለሁ። በዕንጨት ፈንታ ናስ በብረትም ፈንታ ድንጋይ አመጣልሻለሁ። ሰላምን ገዥሽ፣ ጽድቅንም አለቃሽ አደርጋለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements