Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 57:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከሰማይ ልኮ ያድነኛል፤ የረገጡኝን ያዋርዳቸዋል፤ ሴላ እግዚአብሔር ምሕረቱንና ታማኝነቱን ይልካል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እቅዱን በእኔ ላይ ወደሚፈጽመው አምላክ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጮኻለሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እግዚአብሔር ከሰማይ ልኮ ያድነኛል፤ የሚያስጨንቁኝንም ያዋርዳቸዋል፤ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ፍቅሩንና ታማኝነቱን ይገልጣል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ኀጥ​ኣን ከማ​ኅ​ፀን ጀም​ረው ተለዩ፤ ከሆ​ድም ጀም​ረው ሳቱ፥ ሐሰ​ት​ንም ተና​ገሩ።

See the chapter Copy




መዝሙር 57:3
14 Cross References  

እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አትንፈገኝ፤ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ፤


ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፤ ወደ ተቀደሰው ተራራህ፣ ወደ ማደሪያህ ያድርሱኝ።


ጴጥሮስም ሲረጋጋ፣ “ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና አይሁድ ካሰቡብኝ ሁሉ እንዳወጣኝ አሁን ያለ ጥርጥር ዐወቅሁ” አለ።


በእግዚአብሔር ፊት ለዘላለም ይንገሥ፤ ይጠብቁት ዘንድ ምሕረትህንና ታማኝነትህን አዘጋጅለት።


ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ይነሣል፤ ያደነውን እስኪያነክት፣ የገደለውንም ደም እስኪጠጣ፣ እንደማያርፍ አንበሳ ሆኖ ይነሣል።”


ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጥቶ ነበር፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መጣ።


የቤቴ ሰዎች፣ ‘ከኢዮብ ከብት ሥጋ አስቈርጦ፣ ያልጠገበ ማን ነው?’ ብለው ካልሆነ፣


እግዚአብሔር በእኔ ላይ ያለውን ዐላማ ይፈጽማል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ ለዘላለም ነው። የእጅህንም ሥራ ቸል አትበል።


እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሰላምን መሠረትህልን፤ የሠራነውንም ሁሉ አንተ አከናወንህልን።


Follow us:

Advertisements


Advertisements