Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 4:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እግዚአብሔር ጻድቁን ለራሱ እንደ ለየ ዕወቁ፤ እግዚአብሔር ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እናንት የሰው ልጆች፥ እስከ መቼ ድረስ ክብሬን ታዋርዳላችሁ? ከንቱ ነገርን ለምን ትወድዳላችሁ? ሐሰትንም ለምን ትሻላችሁ?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እግዚአብሔር ታማኞች የሆኑ ሰዎችን ለራሱ እንደ መረጠ ዕወቁ፤ ስለዚህ ወደ እርሱ በምጸልይበት ጊዜ ይሰማኛል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጻ​ድቁ እንደ ተገ​ለጠ ዕወቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ እርሱ በጮ​ኽሁ ጊዜ ይሰ​ማ​ኛል።

See the chapter Copy




መዝሙር 4:3
17 Cross References  

እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ እንድትሄዱና ፍሬ እንድታፈሩ፣ ፍሬያችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ። ስለዚህም አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።


የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው፤ ጆሮዎቹም ለጩኸታቸው ክፍት ናቸው።


ጌታ፣ በእውነት እያመለኩት የሚኖሩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸውና ዐመፀኞችን እየቀጣ ለፍርድ ቀን እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።


ይሁን እንጂ፣ “ጌታ የርሱ የሆኑትን ያውቃል” ደግሞም፣ “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከክፋት ይራቅ” የሚል ማኅተም ያለበት የማይነቃነቅ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሟል።


እርሱም ከክፋት ሊቤዠን፣ መልካም የሆነውን ለማድረግ የሚተጋውን የርሱ የሆነውን ሕዝብም ለራሱ ያነጻ ዘንድ ራሱን ስለ እኛ ሰጥቷል።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ የተቀደሰ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ገንዘቡ ያደረገው ሕዝብ ናችሁ።


አንተ ከእኛ ጋራ ካልሄድህ፣ አንተ በእኔና በሕዝብህ መደሰትህን ሌላው እንዴት ያውቃል? እኔንና ሕዝብህንስ በገጸ ምድር ከሚገኙት ከሌሎቹ ሕዝቦች ሁሉ ልዩ የሚያደርገን ሌላ ምን አለ?”


እናንተ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ፤ ከእኔ ራቁ፤ እግዚአብሔር የልቅሶዬን ድምፅ ሰምቷልና።


ምክንያቱም፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ እንድንመላለስባቸው ያዘጋጀልንን መልካም የሆኑትን ሥራዎች እንድንሠራ በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጠርን የእግዚአብሔር እጅ ሥራዎች ነን።


“በመሥዋዕት ከእኔ ጋራ ኪዳን የገቡትን፣ ቅዱሳኔን ወደ እኔ ሰብስቧቸው።”


እናንተ ቅዱሳኑ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ውደዱት! እግዚአብሔር ታማኞችን ይጠብቃል፤ ትዕቢተኞችን ግን ፈጽሞ ይበቀላቸዋል።


ወደ አንተ በተጣራሁ ቀን፣ ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ በዚህም፣ አምላክ ከጐኔ መቆሙን ዐውቃለሁ።


አፌ የጥበብን ቃል ይናገራል፤ የልቤም ሐሳብ ማስተዋልን ይሰጣል።


በዝርፊያ አትታመኑ፤ በቅሚያም ተስፋ አታድርጉ፤ በዚህ ብትበለጽጉም፣ ልባችሁ ይህን አለኝታ አያድርግ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements